በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ አካል የሆነው የማስ ስፖርት በድሬዳዋ ተካሄደ።
በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በአስተዳደሩ ያዘጋጀውና በርካታ የስፖርት ቤተሰቦችን እንዲሁም ወጣቶችን ያሳተፈ የማስ ስፖርትና የምርጫ ቅስቀሳ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል።
በብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተዘጋጀው መርሀግብር ላይ የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ብህን ጨምሮ በርካታ የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የብልጽግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ክቡር አቶ ሻኪር አህመድ ስፖርት የአካልና የአእምሮ ጤናን ከመጠበቅ ባለፈ ለጋራ ብልፅግናና ለአንድነት ያለውን ፋይዳ የጎላ መሆኑን አንስተው፣ የአስተዳደሩ ህዝብ የፓርቲውን ዓላማ በንቃት እንዲደግፍ ጥሪ አቅርበዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ሀገርን መምራት ከጀመረ ወዲህ እንደሀገር ብሎም እንደ አስተዳደር በሁሉም ዘርፎች በተግባር ተጨባጭ ለዉጥ ማስመዝገቡን ተናግረዋል።
ፓርቲው የህዝብን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በመፍታት እያመጣ ያለዉን ትሩፋቶች መላዉ የአስተዳደሩ ነዋሪ በተገቢዉ በመረዳት ለ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ድምፃቸዉን በመስጠት ለተጀመረዉ የብልጽግና ጉዞ ስኬት የበኩሉን አሻራ ማኖር እንዳለበትም አስታውቀዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ክቡር አቶ አብዲ ሙክታር፣ የብልፅግና ፓርቲ የፌዴራልና የአስተዳደሩ ዕጩዎች፣ አመራሮች እንዲሁም የብልፅግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በማስ ስፖርት ተሳታፊ ሆነዋል።
#prosperity