በጅማ ዞን ኦሞ ናዳ፣ በወሊሶ ከተማ፣ በምስራቅ ወለጋ ሳሲጋ እና በምስራቅ ባሌ ሰውዌና ወረዳዎች የሚገኝ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች በነቂስ በመውጣት ለፓርቲው ያላቸውን ደጋፍ ገለፁ
በጅማ ዞን ኦሞ ናዳ፣ በወሊሶ ከተማ፣ በምስራቅ ወለጋ ሳሲጋ እና በምስራቅ ባሌ ሰውዌና ወረዳዎች የሚገኝ የብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች በነቂስ በመውጣት ለፓርቲው ያላቸውን ደጋፍ በደማቅ ሁኔታ ገልጸዋል።
ሰልፈኞቹ "ብልፅግናን መምረጥ ሰላምን፣ ልማትንና አብሮነትን መምረጥ ነው" የሚሉና መሰል መልዕክቶችን በማንገብ በመጪው 7ኛው አገራዊ ምርጫ የፓርቲው ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ በመምረጥ ድምፃቸውን ለፓርቲው ለመስጠት መወሰናቸውን አስታውቀዋል።
በጅማ ዞን ኦሞ ናዳ ወረዳ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነመራ ቡሊ፣ ፓርቲው ባለፉት አምስት ዓመታት ያስመዘገባቸውን ሁለንተናዊ ድሎችና የወደፊት ራዕዮችን ለተሳታፊዎቹ በዝርዝር አብራርተዋል። አቶ ነመራ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ዓመታት የሀገርን ሉዓላዊነት በማስከበርና የዜጎችን ክብር በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ በማረጋገጥ ረገድ ታላላቅ ድሎች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
የተገኘውን ስኬት ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር የቡድንና የዜጎች መብት እኩል የሚከበርባትን፣ በሁሉም ረገድ ሉዓላዊነቷ የተረጋገጠ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተሰሚነት ያላት ጠንካራ ኢትዮጵያን ለመገንባት ፓርቲው ቆራጥ መሆኑንም አቶ ነመራ አረጋግጠዋል። ብልፅግናን መምረጥ ብዝሃነት የሰፈነባትን፣ ዲሞክራሲያዊትና ሁለንተናዊ ብልፅግና የተረጋገጠባትን ሀገር መገንባት መሆኑን በመጥቀስ፣ ነዋሪዎቹ ድህነትንና ኋላቀርነትን በማሸነፍ አስተማማኝ መዳረሻን ለመፍጠር የፓርቲው ምልክት የሆነውን የስንዴ ነዶ እንዲመርጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ብልጽግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነው
#prosperity