በደሴ ከተማ አስተዳደር "ብልጽግና ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሰትፎና ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የብልፅግና ፓርቲ የአደባባይ የምርጫ ቅስቀሳ ተካሂዷል
በደሴ ከተማ አስተዳደር "ብልጽግና ለሴቶች ሁለንተናዊ ተሰትፎና ተጠቃሚነት" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የብልፅግና ፓርቲ የአደባባይ የምርጫ ቅስቀሳ ተካሂዷል።
የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባልና የደሴ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ክብርት ዶ/ር ማኅተመ ኃይሌ በሰልፉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት የለውጥ ዓመታት ሴቶች በፖለቲካው ውሳኔ ሰጪነት ላይ ያላቸው ተሳትፎ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር የተደረገ ሲሆን፣ በኢኮኖሚው ዘርፍ በንግድ፣ በግብርና፣ በአገልግሎትና በፈጠራ ሥራዎች ላይ ተጠቃሚነታቸው እንዲያድግ ሰፊ ሥራዎች መከናወናቸው ተናግረዎል።
በደሴ ከተማ ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን ድጋፍ ለመግለጽ በአደባባይ የወጡ እናቶችና እህቶች፤ "ቀጣይነቱ ለተረጋገጠ ተሳትፎና ተጠቃሚነታችን ምርጫችን ብልጽግና ነው!" የሚል ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተካሄደው በዚህ የሰልፍ ቅስቀሳ ፓርቲው ባለፉት ዓመታት ያስመዘገባቸውን ስኬቶችና የቀጣይ የልማት ዕቅዶች ለህዝብ ይፋ አድርጓል።
የምርጫ ቅስቀሳው ወቅት ፓርቲው በደሴና በአካባቢው የጀመራቸውን የመሠረተ ልማት፣ የግብርና ምርታማነትና የኢንዱስትሪ ግንባታ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።
በከተማ የሚታየውን የህዝቦች አብሮነት ይበልጥ በማጠናከር፣ ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ፓርቲው ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ቃል ገብቷል።
በከተማዋ ለሚገኙ ሴቶች የሥራ ዕድል ፈጠራንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ አዳዲስ ፕሮጀክቶች እንደሚተገበሩ ተመላክቷል።
በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ምክር ቤት አባል እና የደሴ ከተማ ከንቲባ እንዲሁም ብልጽግና ፓርቲን በደሴ በመወከል ለክልል ም/ቤት እጩ የሆኑት አቶ ሳሙዔል ሞላልኝ ብልጽግና ፓርቲ የህዝብን ጥያቄ መሠረት ያደረገ የለውጥ ጉዞ እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ ነዋሪው ለፓርቲው ምልክት ለሆነው የ''ስንዴ ነዶ'' ድምጹን በመስጠት የጀመረውን የብልጽግና ጉዞ እንዲያፋጥን ጥሪ አቅርበዋል።
የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ዓለማየሁ ብልጽግና ፓርቲ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በወሰዳቸው ስልታዊ እርምጃዎችና በሰራቸው ሰፊ ስራዎች እስካሁን ተጨባጭና ከፍተኛ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
ደሴ ከተማን በመወከል የክልል ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ዶ/ር ሐዋ ወሌ ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በሌሎችም ዘርፎች ያላቸው ድርሻ እንዲጎለብት፣ በኢኮኖሚ ራሳቸውን እንዲችሉና መብታቸው እንዲከበር ብልጽግና ፓርቲ ከመቸውም ግዜ በላይ ይሰራል ብለዋል።
#ምርጫችን_የስንዴ_ነዶ_ነዉ
#ብልፅግናን_ይምረጡ
#ኢትዮጵያ_ወደ_ተምሳሌት_ሀገር