በዛሬው ዕለት በወሊሶ ከተማ እና በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን የብልጽግና ፓርቲን ዓላማና ግብ የሚደግፍ፣ የፓርቲውን የምረጡኝ ቅስቀሳ የሚያጎላ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል
በሰልፉ ላይ የታደሙት የከተማዋና የዞኑ ነዋሪዎች "ብልጽግናን በመምረጥ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ መሠረት እንጥላለን!" በማለት ድምፃቸውን በከፍተኛ መነሳሳት አሰምተዋል።
ብልጽግና የሀገራችንን ብዝኃነት በአንድነት አስተሳስሮ፣ የብሔር ማንነትንና ሀገራዊ አንድነትን ሚዛኑን በጠበቀ መልኩ የሚገነባ ብቸኛው ፓርቲ ነዉ። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያላት፣ በጠንካራ መሠረት ላይ የተገነባችና ለዜጎቿ የምትመች ሀገር እንድትሆን ፓርቲያችን ሌት ተቀን እየሰራ ይገኛል።
የጀመርናቸው የልማትና የለውጥ ስራዎች ሳይቆራረጡ ለትውልድ እንዲሻገሩ የምርጫችን መዳረሻ ብልጽግና ፓርቲ ነው።
ድምፃችን ለብልጽግና!
#prosperity