Prosperity Party

በወልቂጤ ከተማ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ አስመልክቶ የድጋፍ ሰልፍ ተካሔደ

ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት እና ሰባተኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በወልቂጤ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሔደ ነው ።

"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር "በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሔደ ባለው የድጋፍ ሰልፍ ያለፉት ስምንት የለውጥ አመታት ስኬቶችን የሚዘክሩና  የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መልዕክቶች እየተስተጋቡ ይገኛል።

በድጋፍ ሰልፉ ምርጫዬ ብልጽግና ነው፣ትላንትን ማከም ነገን መተለም፣የጸና ሰላም የተቃና ስርዓት፣ከገጠር የተሰናሰለ ከተሜነት እና ሌሎችም መፈክሮች ተስተጋብተዋል።

በድጋፍ ሰልፉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ክብርት ወይዘሮ ፋጤ ስርሞሎ፣በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ( ዶ/ር )፣በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪዎች፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ከፍቸኛ አመራሮች፤ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የጉራጌ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል፣የቀቤና ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ መሀመድአሚን በደዊ፣የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር፣የአበሽጌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ካሱ ጁሃር ጨምሮ የፓርቲው አባላት፣ደጋፊዎች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party