Prosperity Party

በአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ተካሄደ

ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ያስተሳሳረች ኢትዮጵያ 

በአፋር ክልል የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። 

የብልፅግና ፓርቲ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለ7ኛው ሀገራዊና ክልል አቀፍ ምርጫ ያዘጋጀውን ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ይፋ የማድረግና የማስተዋወቅ መርሃ ግብር በታላቅ ድምቀት አካሂዷል። 

በመድረኩ ላይ መልዕክታቸውን ያስተላለፉት  የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር ሀጂ አወል አርባ ፣ፓርቲያችን የአፋር ህዝብን  በሀገር ጉዳይ  ከዳር ተመልካች  ቀጥታ ተሳታፊ እንዲሆን አሰሰችሏል። 

ምርጫው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታና የሕዝብ ሉዓላዊነት በተግባር የሚረጋገጥበት እንዲሆን ትኩረት ተሰቶ እየተሠራ መሆኑን የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ ለህዝቡ ዘላቂ ሰላም ለማፅናት በትጋት እየተሰራ ስሆን በሌላኛው በኩል ኢትዮጵያን ተምሳሌት ሀገር ለማድረግ የተጀመረው ሁለንተናዊ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። 

በለውጡ አመታት የአፋር ህዝብን ጨምሮ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ተረጂነት ለማላቀቅ በብዝሃ-ሃብት የሚታዩ ለውጦችን ማስመዝገብ መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ አንስተዋል። አፋር ህዝብ ከዳር ተመልካችነት ወደ እኩልነት የለውጥ አመታት መሆኑን  ርዕስ መስተዳድሩ ያብራሩ ሲሆን በተለይ የአፋር ህዝብ በለውጡ መንግስት  ትልቅ እድሎች ያገኘ ሲሆን ያገኘውን እድል ወደ ውጤት በመቀየር በርካታ ስኬቶች ማሳከት መቻሉን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጿል። 

የአፋር ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ  መሃመድ ሁሴን አሊሳ  በበኩላቸው፣ ፓርቲው በአካታችነት የሁሉንም ዜጎች ሁለንተናዊ ተሳትፎን መርህ ቅድሚያ በመስጠት  በቃሉ ታምኖ ያስመዘገባቸውን ውጤቶችን በመድረኩ አንፀባርቀዋል። 

የአፋር ህዝብ እና ክልሉ   ከበረሃነት ወደ ምርታማነት መሸጋገራቸውን  የጠቀሱት ኃላፊው፤ ይህንን የብልፅግና ራዕይ ዕውን ለማድረግ፣ በዕውቀትና በተግባራዊ ውጤታማነት የታጀበ አዲስ ማኒፌስቶ ለሕዝብና ለአባላት ይፋ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል። 

በተለያዩ ዘርፎች  የክልሉን የተፈጥሮ ፀጋዎች በማልማት የጠንካራ ሀገር ተምሳሌትነትን ለማጠናከር በፓርቲው የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ መሃመድ ሁሴን ገልፀዋል። 

በአፋር ክልል ባህል እየሆነ የመጣው የስንዴ ምርታማነት ትልቅ ለውጥ ማስገኘት መቻሉ  እና የመደመር እና የብልፅግናና የልዕልና ትርጉም ያለው የፓርቲው መለያ "የስንዴ ነዶ" በመሆኑ  የፓርቲውን ምልክት የማስተዋወቁ መርሃ-ግብር የተለየ እንደሚያደርገው ተገልጿል። 

በመርሃ ግብሩ የክልሉ የዞንና የወረዳ መንግስትና የፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ የፓርቲዉ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተሳትፈዋል። 

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party