በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል
በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን በብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብዱራህማን አህመድ ተናገሩ።
የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሃግብር በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን፣ ጎዴ ከተማ አካሄዷል።
አቶ አብዱራህማን አህመድ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደገለጹት፥ ብልዕጽግና ፓርቲ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በሀገረ መንግሥት ግንባታ የተለያዩ ስኬቶች አስመዝግቧል።
ፓርቲው የሀገሪቱን ዜጎች በሁሉም ዘርፎች የሚያሳትፍ አካታችና አሳታፊ ፓርቲ መሆኑንም ገልጸዋል።
በተለይም በሶማሌ ክልል በለውጡ ዓመታት የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ሥራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ እያከናወነ የሚገኘው የልማት ሥራዎች አበረታች ለውጦች ማምጣታቸውን ገልጸው፥ በክልሉ የተጀመረው ልማት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በምረጡኝ ቅስቀሳው ብልጽግና ፓርቲን በክልልና በፌዴራል ምክር ቤት የሚወክሉ እጩዎች ተገኝተዋል።
በሸበሌ ዞን ጎዴ ከተማ በተካሄደው የምረጡኝ ቅስቀሳ መርሃ ግብር ከከተማዋ ሁሉም ቀበሌዎች የተውጣጡ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።