Prosperity Party

በሰንዳፋ በኬ ከተማ፣ በበራክ እና በአላልቱ ወረዳዎች የተቀናጀ የብልጽግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ በድምቀት ተካሂዷል


በዚህ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ሰፊው ህዝብ ለብልጽግና ፓርቲ ያላቸውን የማይናወጥ ድጋፍ በተለያዩ መንገዶች በአደባባይ መስክረዋል። የታየው እጅግ ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ ብልፅግና ፓርቲ እና ህዝብ እጅና ጓንት በመሆን የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በጽኑ መሰረት ላይ ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን በግልጽ ያሳየ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አወሉ አብዲ እንደገለጹት፣ የሰንዳፋ በኬ ከተማና የአካባቢው ህዝብ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር በመሆን የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ በላቀ ጥንካሬ ማስቀጠል እንዳለበት ገልፀዋል። እንደ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ማብራሪያ፣ ብልፅግና ፓርቲ እና ህዝብ በመተማመን፣ በጋራ ዓላማና በጠንካራ ብሄራዊ አንድነት ላይ የተመሰረተ ስርዓት በመገንባት ማንኛውንም ተግዳሮት በድል መወጣት እንደሚችሉ አረጋግጠዋል።

አቶ አወሉ አብዲ በንግግራቸው የብልጽግና መንግስት ከህዝብ ጋር በቅርበት የሚጓዝ፣ የሀገርን ሰላም የሚያስከብር፣ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥርና የህዝብን የኑሮ ደረጃ በዘላቂነት የሚያሻሽል ኃይል መሆኑን አስገንዝበዋል። በመሆኑም ህዝቡ ከመንግስት ጎን በጽናት በመቆም ሰላምን በመጠበቅ፣ በልማት ስራዎች ላይ በንቃት በመሳተፍ እና መንግስትን በመደገፍ ታሪካዊውን የብልጽግና ጉዞ ከግብ ለማድረስ ግንባር ቀደም ድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ደረጃ አርአያ ወደሆነች ከፍታ ለማሸጋገር መንግስትና ህዝብ ተናበዉ መስራት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ፣ ሰላም ካለ ልማት እንደሚኖርና ልማት ሲኖር ደግሞ የህዝብ ህይወት እንደሚለወጥ የሚገልጽ ጥልቅ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ባለፉት ጥቂት አመታት መንግስት እጅግ ፈታኝ ሁኔታዎችን በማለፍ በርካታ ግዙፍ የመሰረተ ልማት ስራዎችን በማከናወን የህዝብን ህይወት በመለወጥ ረገድ አርአያነት ያላቸውና ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውንም አቶ አወሉ አክለው ገልጸዋል።

የሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አለማየሁ ቶንኮሉ በበኩላቸው፣ የለውጥ መንግስቱ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ የህዝብን ኑሮ ለማሻሻል ልዩ ትኩረት በመስጠት ግዙፍ ፕሮጀክቶችና ውጤታማ ኢኒሼቲቮች ተቀርጸው መጠነ ሰፊ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን አብራርተዋል። ወደፊትም እነዚህን ስኬቶች በላቀ ደረጃ ለማስቀጠልና ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት በታቀደው መሰረት በቁርጠኝነት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

 ባለፉት አመታት የተከናወኑት ስራዎች የህዝብን ህይወት ከመሰረቱ በመለወጥ ረገድ ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ ሲሆን፣ ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ለኢኮኖሚ እድገት ማዕከል በማድረግ ረገድ ታላቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙም ተገልጿል።

በመጨረሻም፣ የሰንዳፋ በኬ ከተማ ህዝብ በዕለቱ የነበረውን ከፍተኛ መነሳሳት ወደ ድምጽ በመቀየር የብልጽግና ፓርቲን እንዲመርጥና የጀመረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል። የፓርቲው መለያ ምልክት የሆነው "የስንዴ ነዶ" በምርጫው ቀን የህዝቡ ቀዳሚ ምርጫ እንደሚሆንም ተመልክቷል።

ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party