Prosperity Party

በሮቤ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምረጡኝ ዘመቻ መርሃ ግብር በደማቅ ሁኔታ ተከናወነ

"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌትሀገር!" በሚል መሪ ቃል፣ በመላዉ ሀገር የተጀመረዉ የብልፅግና ፓርቲ የምረጡኝ ቅስቀሳ መረሃ ግብር በሁሉም የኦሮሚያ አካባቢዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚሁ መሰረት በባሌ ዞን ኦና በሮቤ ከተማ አስተዳዳር ቅንጅት ከትላንት ዋዜማዉ ጀምሮ የተዘጋጀዉ የምረጡኝ ቅስቀሳ መረሃ ግብር ዛሬም ቀጥሎ ዉሏል፡፡
በመድረኩ የተገኙት የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ የአደረጃጃት ዘርፍ ሃላፊ መንግስቱ በቀለ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ብልፅግና ፓርቲ በውስጥ ትግልና በብዙ ዜጎች መስዋዕትነት የተወለደ፣ ለዘመናት ለትውልድ ሲንከባለሉ የነበሩ የዲሞክራሲ፣ የእኩልነትና የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄዎችን በመደመር እሳቤ የመለሰ የህዝብ መሰረት ያለው ፓርቲ መሆኑን ተናግረዋል። ፓርቲው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ከድል ወደ ድል እየተሸጋገረ፣ ላለፉት ስምንት ዓመታት በስኬት መጓዙንም ገልጸዋል።
ለሀገር ግንባታ ምሰሶ የሆኑ ትክክለኛ እይታዎችንና አስተሳሰቦችን ይዞ በመደመር እሳቤ ጉዞ የጀመረው ብልፅግና ፓርቲ፣ የልዩነትና የግጭት መንስኤ የሆኑ የተሳሳቱ ትርክቶችን በማስወገድ በዜጎች መካከል ፍቅርና እውነተኛ ወንድማማችነት እንዲሰፍን በማድረግ የኢትዮጵያ የፖለቲካ መረጋጋት እንዲረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ዶክተር መንግስቱ አብራርተዋል።
በዚህ ሂደት ውስጥ የባሌ ህዝብ ከለውጡ ጎን በመሆን ከጥንቱ የኦሮሞ ትግል ጀምሮ እስካሁን እያሳየ ያለው ጀግንነት ለስርአቱ መጠናከር እንደ ሀውልት የሚታይ መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህ ቀጣይነት እንዲኖረው ምርጫዉ ብልፅግና ሊሆን እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። አክለውም የባሌ ህዝብ የለውጡ ባለቤትና የሰላም አምባሳደር መሆኑን በተግባር ሲያሳይ የቆየ በመሆኑ፣ ድምፁን ለብልፅግና በመስጠት ይህንን በድጋሚ ማረጋገጥ እንዳለበት አሳስበዋል።
ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!
ምልክቶችን የስንዴ ነዶ ነዉ!

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party