በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ እና ሰንዳፋ በኬ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ተካሄደ
በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ እና በሰንዳፋ በኬ ከተማ "ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!" በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ንቅናቄ በሰፊ የህዝብ ተሳትፎ ተካሂዷል።
በዕለቱ በተካሄደው የድጋፍ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደገለጹት፤ የብልጽግና ፓርቲ መንግስት ካመጣቸው ለውጦች መካከል የምርትና ምርታማነት መጨመር፣ የኢኮኖሚ መሻሻል እና የዜጎች መብት መከበር ዋነኞቹ ናቸው። በተለይም በግብርናው ዘርፍ በክረምት ዝናብ ላይ ብቻ የነበረውን ጥገኝነት በማስቀረት፣ በመስኖ ስንዴ ልማት የታየው ውጤት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረጉ ተገልጿል።
የሰንዳፋ በኬ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ ከተማቸው የንግድ ማዕከል ብቻ ሳትሆን የምርት መዳረሻም እንድትሆን ፓርቲው ባደረገው ጥረት መደሰታቸውን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በዕርዳታ ስም ብቻ የሚታወቀውን ስንዴ አሁን ላይ በሰፊው በማምረት ለገበያ ማቅረብ መቻላቸው ለፓርቲው ያላቸውን ድጋፍ እንዲያጠናክሩ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።
ተሳታፊዎቹ "ድምጻችን ለብልጽግና ፓርቲ ነው!" በማለት ያላቸውን አጋርነት ያሳዩ ሲሆን፣ የፓርቲው የምርጫ ምልክት የሆነውን "የስንዴን ነዶ በማሳየት ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ብልፅግናን ይምረጡ!
ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!
#prosperity