Prosperity Party

በሚዛን አማን ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው

የብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚያደርገውን የይምረጡኝ ቅስቀሳ መርሃ ግብር በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች በደማቅ ሁኔታ እያካሄደ ይገኛል።
​ፓርቲው ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! በሚል መሪ ቃል እያከናወነ በሚገኘው በዚህ የቅስቀሳ መርሃ ግብር፣ በሁሉም ቀበሌዎች የተለያዩ የአደባባይ ኩነቶችን እየተካሄደ ይገኛል።
​በቅስቀሳ መርሃ ግብሩ ላይ ፓርቲው ባለፉት የለውጥ ዓመታት ያከናወናቸው የልማት ስራዎችና የተመዘገቡ የመልካም አስተዳደር ድሎችን የሚያስታውሱ መልዕክቶች እየተስተጋቡ ይገኛሉ። የተለያዩ መፈክሮችን በማንገብ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች በከተማዋ አደባባዮችና መንደሮች ደማቅ የቅስቀሳ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው።
​የብልፅግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ምልክት የሆነውን ''የሰንዴ ነዶ'' አስመልክቶ በቅስቀሳው ወቅት ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የመደመር፣የአንድነት እና የትብብር መገለጫ መሆኑ በይፋዊ መርሃ ግብሩ ላይ ተመላክቷል።
​በዚህ ሰፊ የቅስቀሳ ዘመቻ ላይ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ከተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች የተወጣጡ አባላት በንቃት እየተሳተፉ ይገኛሉ። መርሃ ግብሩ የፓርቲውን የፖሊሲ አማራጮችና የቀጣይ የልማት እቅዶች ለህዝቡ በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተገልጿል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party