Prosperity Party

በሀረሪ ክልል እና በድሬደዋ አስተዳደር አመራሮች መካከል የ"ህዝብ ለህዝብ" የስፖርት ውድድር በሀረር ከተማ መካሄድ ጀመረ

በሀረሪ እና በድሬደዋ አስተዳድር  ከፍተኛ አመራሮች መካከል የሚካሄድ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስፖርታዊ ውድድር በታሪካዊቷ የሀረር ከተማ በድምቀት መካሄድ ጀመረ።

ይህ ስፖርታዊ ጫዋታ በሁለቱ ጎረቤት ህዝቦች መካከል ያለውን ታሪካዊ ወንድማማችነት ይበልጥ ለማጠናከር እና ሀገራዊ አንድነትን ለማሳደግ ያለመ ነው።

ውድድሩ በሁለቱ ህዝቦችና አመራሮች መካከል ያለውን ትስስር፣ ሰላምና አብሮነት በስፖርታዊ ጨዋነት ማሳደግ ያለመ ነው።

 መጪው 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ስኬታማ እንዲሆን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን በማጠናከር ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ይሆናል

በውድድሩ የተሳተፉ  የሁለቱ ክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንደገለጹት፣ ስፖርት ከውድድር ባለፈ የልብ ለልብ ትስስር መፍጠሪያ ድልድይ ነው።

ይህ ውድድር በሜዳ ላይ የሚደረግ ጨዋታ ብቻ ሳይሆን፣ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን ዘላቂ ሰላምና የልማት አጋርነት የምናረጋግጥበት መድረክ ነው"

ጨዋታው ምርጫውን ተከትሎ ሊመጡ የሚችሉ ልዩነቶችን በውይይትና በስፖርታዊ ጨዋነት ለመፍታት መነሳሳትን መፍጠሩ።

በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለውን ባህላዊና ማህበራዊ እሴት ይበልጥ ማስተዋወቁ።

ይህ በሀረር ከተማ የተጀመረው ስፖርታዊ መርሃ-ግብር በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።

#Prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party