ስንዴ እና የሀይል ሚዛን
ስንዴ ከምግብነት ባለፈ የአንድ ሀገር የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የፖለቲካ ነጻነት መከታና የብሄራዊ ደህንነት ዋስትና ተደርጎ የሚወሰድ ስልታዊ መሳሪያ ነዉ፡፡ ይህ ሰብል በአለም አቀፍ ጂኦ ፖለቲካ መድረክ ላይ የሀይል ሚዛንን የመቀየር አቅም ያለዉ መሆኑን ራስን በስንዴ መመገብ ማለት ከተረጂነት መላቀቅና በአለም አቀፍ ድርድር ወቅት የማንም ተጽእኖ ሳያርፍበት በራስ የመወሰን መብትን መጎናጸፍ ማለት ነዉ፡፡ በመሆኑም ስንዴን በስፋት ማምረት የህዝብን የምግብ ዋስትና ከመጠበቅ ባለፈ ድህነትን እንደ ፖለቲካዊ መሳሪያ ለመጠቀም የሚሞክሩ ኃይሎችን ሴራ ለማክሸፍና የኢኮኖሚ ጥገኝነትን የሚሰብር የድል ጎዳና ነዉ፡፡