Prosperity Party

ሰላምን በሰላማዊ መንገድ!

ግጭትን በኃይል/በግጭት ማሸነፍ ይቻል ይሆናል። ሰላም ግን የሚረጋገጠው በሰላማዊ መንገድ እንደሆነ ብልፅግና ያምናል። ለትውልድ የሚተርፍ ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር የሚቻለው በሀገራችን ለግጭት አዙሪት ምክንያት የሆነውን ቂምና ቁርሾ ለመስበር ሲቻል ነው። ብልፅግናም የግጭት አዙሪትን መስበር እና ሰላምን ማረጋገጥ የምንችለው የአሸናፊ ተሸናፊ፣ የቂም እና የቁርሾን፣ የብሶትና የትካዜን ፖለቲካ መስበር ስንችል እንደሆነ ፅኑ እምነት አለው፡፡ 

ለዚህ ደግሞ የዕርቅና የሰላም መንገድን መከተል ምትክ የለሽ እንደሆነ በማመን ያንን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል። ሰላምን የሚያደፈርሱ ኃይላትን በሕግ ማስከበር ለመግታት ብቻ ሳይሆን ለግጭት ምክንያት የሆኑ አለመግባባቶችን በውይይትና በንግግር ለመፍታት ይሠራል።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር
ብልፅግናን ይምረጡ!

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party