የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛዉ ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ መወዳደሪያ ምልክትና ማኒፌስቶ ይፋ ማድረጊያ ስነስርዓት እየተካሄደ ነዉ
ብልጽግና ፓርቲ በመጪው ግንቦት ወር ለሚካሄደው 7ኛ ጠቅላላ ሃገራዊ ምርጫ የሚወዳደርበትን የምርጫ ምልክትና የምርጫ ማኒፌስቶ ለህዝብ ይፋ አድርጓል።
የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አደም ፋራህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራር አባላት በመድረኩ ተገኝተዋል።
ብልጽግና ፓርቲ ለ7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ የሚወዳደርበት ምልክት "የስንዴ ነዶ" ሲሆን: "ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር" የምርጫው መሪ መልዕክትነት እንደተሰየመም በመድረኩ ተገልጿል፡፡
የስንዴ ነዶ የመደመር፣ የአንድነትና የትብብር ተምሳሌትነትን የሚወክልና የምርታማነት መገለጫ እንደሆነም ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመጪው ግንቦት 24/2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁ ይታወሳል።