Prosperity Party

የብልጽግና ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች እያካሄደ ያለው የ"ምረጡኝ" ቅስቀሳ ዘመቻ በደማቅ ሁኔታ ቀጥሏል

በምስራቅ ቦረና፣ በቄለም ወለጋ ዳሌ ሰዲ እና በቡኖ በደሌ ጮራ ወረዳዎች የተካሄዱት እነዚህ መርሐ ግብሮች የፓርቲውን ግዙፍ የልማት ስኬቶችና የወደፊት ተስፋዎች ለህዝቡ ይፋ ያደረጉ ነበሩ። በምስራቅ ቦረና ዞን የተከናወነው ስፖርታዊ ንቅናቄ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች የታየው ከፍተኛ የህዝብ ትዕይንት  ፓርቲው ያስመዘገባቸውን ዘርፈ ብዙ ድሎች ህብረተሰቡ በውል የተረዳው መሆኑን ማሳያ ሆኗል።

በእነዚህ ታላላቅ መድረኮች ላይ የታደመው ህዝብ እንደገለጸው፣ ብልጽግና ፓርቲ ሀገሪቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገሩ የልማት ስራዎችን በተጨባጭ ማከናወን ችሏል። ባለፉት ዓመታት የታዩት የኢኮኖሚ መነቃቃቶች፣ የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችና ማህበራዊ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ብልጽግና ብቸኛውና ትክክለኛው ምርጫ መሆኑን ደጋፊዎቹ አረጋግጠዋል። በተለይም እውነተኛ ፌዴራሊዝምን ከማስፈንና በህዝቦች መካከል ያለውን ወንድማማችነት ከማጠናከር ባሻገር፣ ለዘላቂ ሰላም ግንባታ የሚከናወኑ ተግባራት የሀገሪቱን የወደፊት ብሩህ ተስፋ የሚያለመልሙ መሆናቸው በስፋት ተነስቷል።

እነዚህ የልማትና የሰላም ስራዎች የነገዋን ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ የሚወስኑ መሆናቸውን የተረዱት ደጋፊዎቹ፣ የጀመሩትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉና በምርጫውም ፓርቲውን እንደሚመርጡ ቃል ገብተዋል። ብልጽግና ፓርቲን በመምረጥ ኢትዮጵያን የሁለንተናዊ ብልጽግና ተምሳሌትና ለሌሎችም አርአያ የምትሆን ሀገር ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም ቃል ገብተዋል።

ብልጽግና ፓርቲን ይምረጡ!
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party