Prosperity Party

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በሶማሊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ያስገነባውን 15 የመኖሪያ ቤቶችን አስረከበ

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት በጅግጅጋ ከተማ ለአቅመ ደካማ አካል ጉዳተኞች ያስገነባውን 15 ዘመናዊ ቤቶችን ከነ ሙሉ የቤት ቁሳቁስ ለተጠቃሚዎች በዛሬው ዕለት አስረክቧል፡፡

የመኖሪያ ቤቶቹ ለነዋሪዎቹ ተላልፈው በተሰጡበት መርሐግብር ላይ የተገኙት የሶማሊ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ ፓርቲው በርካታ ሰው ተኮር ልማቶችን ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ላይ ይገኛል ብለዋል ።
ይህ አይነት አቅመ ደካማ ዜጎችን በተለይም አካል ጉዳተኞችን ትኩረት መስጠት በህዝቦች መካከል የኖረውን የመደጋገፍ ባህልን እንደሚያጠናክር የገለፁት ኃላፊው እንደ ክልል ይህን መሠል ስራዎች ለማስቀጠል እንደሚሰራም ገልፀዋል ።
የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሀብት አስተዳደር ዘርፍ ሀላፊ አቶ ብርሃኑ ፈይሳ በበኩላቸው በዛሬው ዕለት በብልፅግና ፓርቲ ተገንብተው ለአካል ጉዳተኞች ተላልፈው የተሰጡት መኖሪያ ቤቶች የፓርቲውን ሰው ተኮር ተግባራትን የሚያሳይ ነው ብለዋል ።
የብልፅግና ፓርቲ እንዲህ አይነት የህብረተሰቡን የመኖሪያ ቤቶች ለህብረተሰቡ ተላልፎ በተሰጠበት ፕሮግራም ላይ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሀብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ፈይሳ ፣ የሶማሊ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊ ኢ/ር መሀመድ ሻሌ ፣ የጅግጅጋ ከተማ ከንቲባ ኢ/ር ሻፊ አህመድ እና ፣ ሌሎች አመራሮች ተገኝተዋል ።
የመኖሪያ ቤቶቹን የተረከቡት የጅግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች የብልፅግና ፓርቲ ዘመናሪያ ቤቶችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party