When the going gets tough, the tough get going
“When the going gets tough, the tough get going” የሚለው የውጭ ምሳሌያዊ አነጋገር፣ ፈተና ስብራት ሳይሆን የስኬት ምንጭ መሆኑን ያስገነዝብናል፡፡ ማንኛውም ታላቅ ስኬት የሚገኘው አልጋ በአልጋ በሆነ መንገድ ሳይሆን፣ ፈተናን ወደ ዕድል በመለወጥ ጥበብ መሆኑን በግልጽ እንረዳለን። ፈተና የሂወት ሂደት አካል እንጂ እንቅፋት አለመሆኑንና እንደውም አብዛኛውን ጊዜ ፈተና የስኬት ምንጭ መሆኑን እናያለን፡፡
የብልፅግና ፓርቲ ጉዞም በትክክል የዚህ ፈተናን ወደ ዕድል የመቀየር ፍልስፍና በመከተል በርካታና ግዙፍ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል። የፓርቲያችን ስኬት የሚታየው በሰላም ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራዊና ክልላዊ ፈተናዎች ሲደራረቡ እንኳን አይበገሬነትን በማሳየት፣ የለውጥ አጀንዳውን ወደፊት ማስቀጠል በመቻሉ ነው። ፓርቲያችን የተጋረጡበትን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች በመቋቋምና በመቀልበስ፣ ለሌሎች አገሮች ጭምር እንደ የጽናትና ስኬት ተምሳሌት ሆኖ መታየት ችሏል፡፡
የፓርቲያችንን ጥንካሬ ከሚያሳዩ ቁልፍ መገለጫዎች አንዱ የፀደቀው የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅዱ ነው። ይህ ዕቅድ "ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግሥት እና ለጠንካራ ሀገር" በሚል መርህ የተመሰረተ ሲሆን፣ የለውጥ ቀጣይነትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ያለመ ነው።ይህ ስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ ብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን የተሟላ ሉዓላዊነት እና የፖሊሲ ነጻነትና ሀገራዊ ክብርን ለማስጠበቅ የሚደረገውን ሁሉን አቀፍ ጥረት የሚያሳይ የቁርጠኝነት ማሳያ ነው።
ብልጽግና በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጋርጠውበት የነበሩት ከፖለቲካዊ ሴራ እስከ ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችና ፈተናዎች በአይበገሬነት በመቋቋም ፈተናዎችን ወደ ለውጥ የመለወጥ ድንቅ ብቃትን አሳይቷል። ፈተናዎች የብልፅግናን ፓርቲን መርሆች የሸረሸሩ ሳይሆን፣ ይልቁንም አይበገሬነቱን ያጎሉ ናቸው። ፓርቲው የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል፣ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ እና የሀገርን ኢኮኖሚያዊ መሰረት ለማጠናከር በሚያደርገው ጥረት፣ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚመጡ ጫናዎችን በብቃት ተቋቁሟል፣ ይህም የፓርቲያችንን የአስተሳሰብ ብቃትና ብስለት አመላክቷል።
ፓርቲያችን ብልጽግና ፈተናዎችን ወደ ስኬት የመቀየር ጥበብ በመጠቀም በአጭር ጊዜ ውስጥ በልማት፣ በዲፕሎማሲ እና በተለያዩ ዘርፎች ያስመዘገብናቸው ስኬቶች የፓርቲያችንን ብቃት የሚያሳዩ ከመሆናቸውም በላይ የወደፊቷ ኢትዮጵያ በብልጽግና እጅ በርካቶች የሚቀኑባትና ምስሌ የሚያደርጓት እንደሆነች ከወዲሁ ማየት ይቻላል፡፡