Prosperity Party

"ኮሚሽኑ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት እየተደረገ በሚገኘው ሂደት እሴት የሚጨምሩ ግኝቶችን ከምክረ ሃሳብ ጋር ለፓርቲው በመስጠት ውጤታማ ተግባራትን አከናውኗል"- ደስታ ተስፋው (ዶ/ር)

የብልጽግና ፓርቲ ኢንስፔክሽን እና ስነምግባር ኮሚሽን 9ኛ የጋራ ግምገማ መድረክ በድሬደዋ አስተዳደር እየተካሄደ ይገኛል። 

መድረኩን በንግግር የከፈቱት ዋና ኮሚሽነር ክቡር ዶክተር ደስታ ተስፋው 'እንኳን ኢትዮጵያዊያን ወደ ትንሿ ኢትዮጵያ ወደሆነችው ድሬደዋ አስተዳደር በሰላም መጣችሁ' በማለት ኮሚሽኑ የፓርቲውን ጤንነት በማስጠበቅ፣ የአባላት መብቶችና ጥቅሞች መከበራቸውን ክትትል በማድረግ እና የፓርቲ ሀብትና ንብረት ለታለመለት አላማ መዋሉን ቁጥጥር የማድረግ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ አትኩሮ የሚሰራ የፓርቲው ተቋማዊ መዋቅር መሆኑን ጠቅሰዋል። 

አክለውም ኮሚሽኑ ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት እየተደረገ በሚገኘው ሂደት የራሱን ተቋማዊ አደረጃጀትና አሰራር በመዘርጋት ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። 

በመድረኩ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የድሬደዋ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ ክቡር አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ የሰላም፣ የመቻቻልና አብሮነት ማሳያ ወደሆነችው ትንሿ ኢትዮጵያ ወደሆነችው ድሬዳዋ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል። 

በማስከተል ብልጽግና ፓርቲ በአሰራርና አደረጃጀት እራስን በማጠናከር ጠንካራ ፓርቲ ለመገንባት እያደረገ ለሚገኘው ጥረት የኮሚሽኑ ሚና ከፍ ያለ መሆኑን በመጥቀስ መልካም የውይይትና ቆይታ ምኞታቸውን ገልፀዋል። 

የኮሚሽኑ ፀሐፊና ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሀብታሙ ሲሳይ እንኳን በደህና መጣችሁ መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት እንደገለጹት ይህ መድረክ በ2018 በጀት ዓመት በእቅድ ከተያዙ  ተግባራት መካከል በግማሽ አመቱ የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ለማድረግ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰዋል። 

በመድረኩም የየክልኩ የኮሚሽኑ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊወች ሪፖርት እየቀረበ ነው።

በመድረኩ የብልፅግና ኮሚሽን አባላት፣ የክልል፣ ከተማ አስተዳደሮችና የፌደራል አደረጃጀት የኮሚሽኑ አመራሮች ተገኝተዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party