Prosperity Party

"በወንድማማችነት እሴት ላይ የቆመ ህብረ ብሔራዊ አንድነት መገንባት "

በኢትዮጵያ የወንድማማችነት እሴትን ለማጎልበት ፓርቲያችን የመደመር መንገድን ይከተላል፡፡ ፓርቲያችን ብልፅግና የመደመር እሳቤዎችን አንድ በአንድ እየተገበሩ በመሄድም የወንድማማችነት መንፈስን ከተኛበት የሚቀሰቅስ ፓርቲ ነው።

"የብሔሮችን ጥያቄ ያከበደው የወንድማማችነት መቅለል ነው"ብሎ የሚያምነው ፓርቲያችን የብሔሮችን ጥያቄ የሚፈታው በወንድማማችነት ማዕቀፍ በመሆኑ ለዚህ ገቢራዊነት ይተጋል፡፡

በሕብረ - ብሔራዊነት ታሪካዊ ነባራዊ በደሎችን ፤ መስተካከልና መታረም ያለባቸውን የተዛቡ፣ ኢ-ፍትሃዊ ግንኙነቶች በማረም ህብረትና ወዳጅነትን የሚያጠናክር እና ብዙ ሆነን እንደ አንድ፣ አንድ ሆነንም እንደ ብዙ የምንቆምበት ፣ ለጋራ ዓላማና ግብ አብረን የምንተጋበት ፣ እጣ ፈንታችንም እጅጉን የተቆራኘ መሆኑን አብረን መስራት እንዳለብን በመገንዘብ ለወንድማማችነት መጎልበት ይሰራል፡፡

በተለይም በሀገራችን ለዘመናት የህዝቦች የእኩልነት ጥያቄዎች በህዝቦች በወንድማማችነት እሴት ላይ የቆመ ህብረ ብሔራዊ አንድነት መገንባት ፓርቲያችን ትኩረት የሚያደርገውና ሊያሳካ የሚፈልገው ቁልፍ ጉዳይ ነው። ይህም ብዝሃነታችንን የሚቀበልና የሚደግፍ ሥርዓት መፍጠር እና በዚያው ልክ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ጠንካራ የሚያደርግ ሥርዓት በመገንባት ነባራዊ ሁኔታ ላይ ነው፡፡ መራር መስዋትነት ህገ መንግስታዊ እውቅና እንዲያገኝ የተደረገው የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በህገ መንግስቱ የተቀመጡ መብቶች ያለምንም መሸራረፍ ተፈጻሚ እንዲሆኑ ፓርቲያችን ይሰራል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ የወንድማማችነትን ጉዳይ ዓላማው አድርጎ በመንቀሳቀስና ዜጎችን በወንድማማችነት የሚያሰልፈውን ጎዳና በመከተል ህዝቦች በወንድማማችነት እንዲቆሙና የአንዱን ችግር እንዲረዳ በማድረግ ነባር ችግሮችን በይቅርታ መንገድ ስብራትን በመጠገን ፣በህብረ ብሔራዊነትና በወንድማማችነት መንፈስ በብሔራዊ አርበኝነት ትጋት እና በወል ትርክት ላይ በተመሰረተ መግባባት የበለፀገች ህብረ ብሔራዊት ኢትዮጵያን በሁሉም ህዝቦች ተሳትፎ ለመገንባት ይሰራል፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party