Prosperity Party

ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት በርካታ ፖለቲካዊ፣ ተቋማዊ እና ህጋዊ ማሻሻያዎችን ተግብሯል

ያልተቋጨዉን የሀገረ መንግስት ግንባታ ለማፋጠን እና ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠር ሀገራዊ የምክክር መድረኮችን በማመቻቸት፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን በመንግስት መዋቅር ውስጥ ማሳተፍ፣ የዲሞክራሲ ተቋማትን ገለልተኝነት ለማረጋገጥ የተወሰዱ እርምጃዎችና ሌሎችን መጥቀስ ይቻላል።

የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት በተወሰዱ እርምጃዎች ነፍጥ አንግበው ሲታገሉ ከነበሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ፣የሞት ፍርደኛ፣ በየፖለቲካ አመለካከት ያላቸው  በእስር ላይ የነበሩ ሁሉ እንዲፈቱ፣ በዲሞክራሲ ምህዳሩ ጥበት ተገፍተዉ ከሃገራቸው የተሰደዱ የፖለቲካ ሃይሎችና ዜጎች ሁሉ ወደ ናፈቋት እናት ሀገራቸው ኢትዮጵያ እንዲገቡና የአዲሱ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ እንዲሳተፉ ተደርጓል።

ፓርቲያችን በ6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በህዝብ ድምፅ አሸናፊ ሆኖ መንግስት ቢመሰርትም ሀገር የጋራ በመሆኑ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በጠላትነት የመፈረጅ ኋላ ቀር የፖለቲካ ባህል በመሻገር የተፎካካ ፓርቲ አመራሮችን  ከሚኒስት መስሪያቤቶች እስከ ወረዳ ድረስ ባሉ የመንግስት መዋቅር ዉስጥ አመራር ሆነዉ ህዝብ እንዲያገለግሉ ከማድረግም ባሻገር አብሮ መስራት እንደሚቻልና አካታችና አቃፊነቱንም በተግባር የገለፀ ተራማጅ ፓርቲ ነዉ።

እኛ ብልፅግናዎች በሀገር በቀሉ መደመር እሳቤ እየተመራን የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሁለንተናዊ ብልፅግናን እዉን ማድረግን መዳረሻችን አድርገን፤ የገጠሙንን ፈተናዎች ወደ እድል በመቀየር ለሀገራችንና ለህዝባችንን ትልቅ ራዕይ ሰንቀን በአንድ እጁ ሰላምን ለማፅናት፤ በሌላዉ እጅ ደሞ ልማት ለማረጋገጥ በፈጠራ፣ በፍጥነትና ዝላይ መርሆች በፈጣን በቡር በትክክለኛ ሀዲድ ላይ እየተጓዝን እንገኛለን።

ብልፅግና ቃልን በተግባር የሚፈጽም፣ በፈተናዎች ውስጥ ጸንቶ ውጤት የሚያስመዘግብ እና ሁሉንም ኢትዮጵያውያን በእኩልነት የሚያቅፍ ብቸኛው  ወጥ ሀገራዊ ፓርቲ ስለሆነ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር ብልፅግና ፓርቲን ይምረጡ!

ምልክታችን የስንዴ ነዶ ነዉ!

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party