መልካም የዘራ መልካም ምርት እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አሽክላ የዘራውም አሜኬላ ያጭዳል። ስለተመኘን ብቻ አሜኬላው በመልካም ስብል አይለወጥም። በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊ ጉዳዮች ውስጥ የሥራ ውጤቶች ናቸው። ስለዲሞክራሲም ስናስብ ይህንን ሐቅ መዘንጋት የለብንም። የምንገነባው ሕጋዊና ሕዝባዊ መንግሥት የሚወሰነው በቅድመ ምርጫ ተሳትፎአችን ልክ ነው። ተሳትፎአችን ከጠነከረ ዲሞክራሲያችንም ይበልጣል። ደካማ ተሳትፎ አድርገን ጠንካራ ዲሞክራሲ ለማሳደግ መመኘታችን ሞኝነት ነው። ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በባዶ መሬት አይበቅልም፤ በጭቅጭቅና ሥርዓት አልበኝነትም አይገነባም። ይልቁንም ስኬትን ለትብብርና ቅንጅት ልብን ክፍት ማድረግን፣ በጨዋታው ሕግ መመራትን ይጠይቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከተናገሩት የተወሰደ
መልካም የዘራ መልካም ምርት እንደሚያጭድ ሁሉ፣ አሽክላ የዘራውም አሜኬላ ያጭዳል። ስለተመኘን ብቻ አሜኬላው በመልካም ስብል አይለወጥም። በመንፈሳዊውም ሆነ በዓለማዊ ጉዳዮች ውስጥ የሥራ ውጤቶች ናቸው። ስለዲሞክራሲም ስናስብ ይህንን ሐቅ መዘንጋት የለብንም። የምንገነባው ሕጋዊና ሕዝባዊ መንግሥት የሚወሰነው በቅድመ ምርጫ ተሳትፎአችን ልክ ነው። ተሳትፎአችን ከጠነከረ ዲሞክራሲያችንም ይበልጣል። ደካማ ተሳትፎ አድርገን ጠንካራ ዲሞክራሲ ለማሳደግ መመኘታችን ሞኝነት ነው። ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት በባዶ መሬት አይበቅልም፤ በጭቅጭቅና ሥርዓት አልበኝነትም አይገነባም። ይልቁንም ስኬትን ለትብብርና ቅንጅት ልብን ክፍት ማድረግን፣ በጨዋታው ሕግ መመራትን ይጠይቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለዒድ አል ፈጥር በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ከተናገሩት የተወሰደ