በምስራቅ ወለጋ ዞን ነቀምት ከተማ በሀገራዊ ለውጡ ለተገኘው ስኬት እውቅና የሚሰጥ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበትን 8ኛ ዓመት አስመልክቶ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ በነቀምት ከተማ በለውጡ ለተገኘው ድልና ስኬት እውቅና የሚሰጥ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ የተገኙ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ባስተላለፉት መልዕክት ከመጋቢት እስከ መጋቢት የተመዘገቡ የስኬት ጉዞዎችን ገልጸው፤ በመጋቢት 24 ተምሳሌታዊ ጉዞ እና መሰረታዊ ርምጃ የተመዘገቡ ስኬቶችን አድንቀዋል።
በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ፣ በቀጣይም የተሻለ ስራ እንዲሰራ ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ የሚያረጋግጡ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛል።