Prosperity Party

የጠራ ሰማይ በሚታይበት፤ የድካም አዝመራ በሚሰበሰብበት የመጋቢት ወር፣ አሻጋሪ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ከፍታዎቻችን አስምረናል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት መጋቢት ለፖለቲካችን የልዩ ታሪክ ወር ነው ብለዋል፡፡

ሕዝብ ከጨለማ ወደ አሻጋሪ ብርሀን የወጣበት የአዲስ ምዕራፍ መክፈቻ ወርም ነው። በመጋቢት አያሌ የለውጥ ነጋሪቶች ተጎስመው አዲስ የፓለቲካ-ኢኮኖሚ ለውጥ ታውጇል።

ሕዝባዊ ግፊት እና ትግል ያመጣው የመጋቢት ለውጥ ኢትዮጵያን ወደ ኋላ ያስቀሩ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ስብራቶችን መጠገን ያስቻሉ ሪፎርሞች የተተገበሩበት ነው፤ የሕዝባችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት የጀመሩበት አዲስ የኢትዮጵያ ንጋትም ሆኗል።

የምርትና ምርታማነት ዕድገት፣ የቱሪዝም መነቃቃት፣ የማዕድን ሐብት ተጠቃሚነት፣ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ፣ የከተማ ልማት እና የዲፕሎማሲ ስኬት ሁሉ ጅማሯቸው መጋቢት ነው፡፡

በተቋም ግንባታም ባለፉት ስምንት ዓመታት አስደናቂ ለውጦች ተመዝግበዋል። የጸጥታና የደኅንነት ተቋማት ታላቋን ኢትዮጵያ የሚመጥኑ እንዲሆኑ በሰው ኃይል፣ በቴክኖሎጂ፣ በአደረጃጀትና በሥራ ከባቢ የማዘመን ሥራዎች በስኬት ተከናውነዋል።

መጋቢት የሀገራችንን ከተሞች የማዘመን ትልም ዕውን የሆነበት፣ የኮሪደር ልማት ስኬቶችን መጎናፀፍ የቻልንበት፣ የዓየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት ያለመ የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻን በቢሊየን የሚቆጠሩ ዛፎችን በመትከል አረንጓዴ ምድር የፈጠርንበት፣ እንዲሁም በሀገራችን አዲስ የፖለቲካ፣ የዴሞክራሲ እና የትርክት ዕይታ የተበሰረበት ወር ነዉ፡፡

ለሺህ ዓመታት በዝናብ ጥገኝነት ላይ ተመስርቶ የነበረውን ግብርናችንን በማዘመን በበጋ መስኖ ዓመቱን ሙሉ ማምረት የጀመርነው በዚሁ ወርሃ መጋቢት ነው፡፡ ኢትዮጵያ በበጋ መስኖ ስንዴ ኢኒሼቲቭ ከውጭ የሚገባ ስንዴን ሙሉ ለሙሉ በማቆም አሁን ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ስንዴ አምራች ሀገር ሆናለች። የወተት፣ የዶሮና የማር ምርቶች በየቤተሰቡ ሌማት ላይ እንዲገኙ የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭ ጅማሮው መጋቢት ነው፡፡

እነዚህ ባለፉት ስምንት ዓመታት ኢትዮጵያን ከውስብስብ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አዲስ የከፍታ ምዕራፍ ካሸጋገሩ ድሎች ጥቂቶቹ ናቸው።

በመሆኑም ለሕዝባችን የላቀ ተጠቃሚነት፣ ለሀገራችን ክብርና ብልፅግና መሳካት አበክረን እንሰራለን ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party