Prosperity Party

ብልፅግና ፓርቲ፤ ወጣቱ የሀገር ግንባታ ዋና ሞተር እና የለውጥ ኃይል መሆኑን በጽኑ ያምናል

ብልፅግና ፓርቲ፤ ወጣቱ የሀገር ግንባታ ዋና ሞተር እና የለውጥ ኃይል መሆኑን በጽኑ የሚረዳ ፓርቲ እነደመሆኑ፤ ወጣትነት እንደ ስጋት የሚታይበት ዘመን አብቅቶ እንደ ታላቅ ጸጋና የብልፅግና አጋር የሚታይበትን ስርዓት እየገነባ ይገኛል፡፡

ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ ቁጥራቸዉ ከ14.4 ሚሊዮን በላይ ለሆኑ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠር ችለናል። ወጣቱን የዓለም አቀፍ የስራ ገበያ በሚጠይቀዉ ልክ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማድረግ በማሰብ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማድረግ የ5 ሚሊዮን ኮደሮች ኢኒሼቲቭን በማስጀመር የዲጂታል ክህሎት ስልጠና እየሰጠንም እንገኛለን።

ለዉጡን ተከትሎ በነበሩት አመታት 25.9 ሚሊዮን ወጣቶች በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ የሀገራቸውን ማህበራዊ ችግሮች በመፍታት ረገድ ታሪክ የማይረሳው አሻራ አኑረዋል። ይህ ተሳትፎ ወጣቱ ለሀገሩ ያለውን ፍቅርና ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየበት ነው።

በቀጣይ፤ ብሔራዊ የወጣቶች ልማት ፈንድ በማቋቋም መንግስት ለወጣቶች የሚያቀርበውን የብድርና የቴክኒክ ድጋፍ እናሰፋለን። ወጣቱን የዲጂታል ኢኮኖሚ ባለቤት ለማድረግ የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን እናስፋፋለን። ተጨማሪ የወጣቶች መዝናኛና የስፖርት ማዕከላት ግንባታዎችንም አስፍተን እንቀጥላለን።

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሃገር፣ ብልፅግናን ይምረጡ!

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party