የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝደንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ
የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዝደንት እና የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት የ መልዕክት ፤የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል መሆኑን ገልጸዋል።
በዓሉ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል። ሠፈሩ ይሰባሰብበታል። ከተማውና አካባቢው ወደ አንድ አደባባይ ይተምበታል ሲሉም ተናግረዋል።
ከእንጨት እስከ ደመራ ያለው መሰባሰብም የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ተምሳሌት ነው ብለዋል።
በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያን ዐቅሞች እያሰባሰብንና እየደመርን ታላቅ ሀገራዊ ዐቅም ለመፍጠር እንትጋ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።