Prosperity Party

7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ፍትኃዊ እንዲሆን ብልፅግና ፓርቲ የበኩሉን ሚና ይወጣል - አቶ አደም ፋራህ

ጥር 07 2018 ዓ.ም

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና /ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የፓርቲው 2018 በጀት ዓመት 6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ላይ እንደገለፁት፥ ሀገራዊ ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን ፓርቲው የበኩሉን ሚና ይወጣል።

የዴሞክራሲ ስርዓትን ለማፅናት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፍትሃዊ ነጻና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፓርቲው አመራሮችና አባላት በቁርጠኝነት እየሰሩ መሆናቸውን ያነሱት አቶ አደም ከዚህ ረገድ ባለፉት ስድስት ወራት የተሰሩ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አስመዝግበዋል ብለዋል።

እንደ ፓርቲ በምርጫው በብቃት ለመሳተፍ ዝግጅቶች መደረጉንም ተናግረዋል።

የፓርቲው 2018 በጀት ዓመት 6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ የሁሉም //ቤቶች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ባለፋት ስድስት ወራት የተከናወኑ የፓርቲ ስራዎች በርካታ ውጤቶች የተመዘገቡበትና ተሞክሮዎችም የተወሰዱበት ነው ብለዋል አቶ አደም ፋራህ።

የልማት ስራዎችን የህዝብን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መንገድ በመምራት  ዘላቂ ሰላምንም ለማረጋገጥ የተደረጉ ጥረቶች ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል።

የፓርቲው ኢኒሼቲቮችና ሰው ተኮር ስራዎች አፈጻጸም የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት እንደሆነ ገልፀው በዚህም የህዝብ ተሳትፎ የላቀ እንደሆነ አብራርተዋል።

በየአካባቢው ያሉ እምቅ አቅሞችን ለይቶ በመጠቀም ለሀገር ኢኮኖሚ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ስኬቶች ተመዝግበዋል።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በማጠናከር ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት/እህትማማችነት ትርክት እንዲጎለብት ተደርጓል በዚህም ሀገራዊ አንድነትን ማጠናከር ተችሏል።

ባለፉት ስድስት ወራት የፓርቲ ዕሳቤዎችን በአግባቡ የተረዳ አመራር ለመፍጠር በተሰሩ ተግባራት የአመራር ብቃት አድጓል በዚህም ፓርቲያችንን በአደረጃጀትና በአሰራር ማጠናከር ተችሏል።

አሰባሳቢ የጋራ ሀገራዊ ትርክትን ከመገንባት አንፃር በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።

አቶ አደም ፋራህ እንዳብራሩት ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ ስኬቶች የፓርቲውን የህዝብ ቅቡልነት ማሳደግ ተችሏል።

ፓርቲው የልማት ስራዎችን በብቃት መምራት በመቻሉ የህዝቡ አመኔታ ጨምሯል። ለዚህም ማሳያው በልማት ስራዎች በቀዳሚነት መሳተፉና ጥያቄዎቹንም በህዝባዊ መድረኮች በግልጽ ማቅረቡ ነው ሲሉ አብራርተዋል።

የብልፅግና ፓርቲ 2018 በጀት ዓመት 6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም የግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ይገኛል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party