Prosperity Party

የአፍሪካ ቀንድን በአካል እና በኢኮኖሚ ይበልጥ ለማስተሳሰር ቁርጠኞች ነን- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)

በዛሬው እለት ታሪካዊ የሆነውን የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ መርቀን ለአገልግሎት አብቅተናል። በሶማሌ ክልል የሚገኘው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት የኃይል ዋስትና የማረጋገጥ ስትራቴጂያችን አንድ የማዕዘን ድንጋይ ነው። ፕሮጀክቱ ዓመታዊ ኃይል የማመንጨት አቅሙ 467 ጊጋ ዋት በሰዓት (GWh) ሲሆን፤ ዘመናዊ SCADA እና SVG ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ለተረጋጋ የኃይል አቅርቦት እና ለቴክኖሎጂ-መራሽ ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

የአይሻ ስትራቴጄያዊ መልክዓ-ምድራዊ አቀማመጥ ከምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የንፋስ ኮሪደርነቱ ያለፈ ጠቀሜታ አስገኝቶለታል። ለጎረቤት ሀገራት ያለው ቅርበት ኢትዮጵያን የምስራቅ አፍሪካ የኃይል ንግድ ማዕከል ለማድረግ ለተቀመጠው ግብ መሳካት በተግባር የተረጋገጠ ትልቅ እመርታ ነው።

በመደመር መርህ የኢትዮጵያን ሰፊ የተፈጥሮ ጸጋ ወደ የጋራ ሐብት በመለወጥ የአፍሪካ ቀንድን  በአካል እና በኢኮኖሚ ይበልጥ ለማስተሳሰር ቁርጠኞች ነን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party