የመራጮች ምዝገባ በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን!
በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን የባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ዘንዘልማ ጢስ ዓባይ ምርጫ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች አንዱ የሆነው የሮቢት ምርጫ ጣቢያ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ነው።
በቀጣናው የመራጮች ምዝገባ በማንዋል የሚካሃድ ሲሆን ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም ዜጋ መታወቂያ በመያዝ ምዝገባውን በማከናወን የመራጭነት ካርድ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።
የሮቢት ቀበሌ አርሶ አደሮች ግንቦት ወር በሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ የመራጭነት ካርድን በማስቀደም ለመምረጥ ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።
“ዘመናዊ ግብርናን በማስፋት ለአርሶ አደሩ ኑሮ መሻሻል ይሠራል ብለን የምናስበውን መንግሥት ለመምረጥ ማሟላት የሚገባንን አዘጋጅተን ምዝገባ እያደረግን ነው” ብለዋል አርሶ አደሮቹ።
ሰላማዊ ምርጫ የሀገርን የወደፊት ተስፋ የሚወስን የዴሞክራሲ ሥርዓት መገለጫ ስለመሆኑ እንደሚገነዘቡም ነው የገለጹት።
ሁሉም አርሶ አደሮች እና ዜጎች በወቅቱ የመራጭነት ምዝገባ በማድረግ ካርዳቸውን እንዲይዙ እና ለምርጫው እንዲዘጋጁም መልዕክት አስተላልፈዋል።