Prosperity Party

አሻጋሪ ህልም ፣ በመደመር አቅም ፣ በላቀ ተግባቦት!

ጥር 03 2018 ዓ.ም

በፈጣን የለውጥ ጉዞ ላይ የምትገኘው አዲስ አበባ የብልፅግና ተምሳሌትነቷን አስፍታ ቀጥላለች። በየቀኑ ማበብ በየቀኑ መፍካት የከተማችን መለያ ከሆኑ ውሎ አድሯል።

የዘመናዊ ከተማነት ባህሪይ ያልነበራት ከተማችን ጥልቅ ጉስቁልና መገለጫዋ የነበረ፣ አይደለም ለዉጪ እንግዶች ለራሳችን ለኢትዮጵያውያንም ጭምር የሚያሸማቅቀ፣ አንዳንድ አፍሪካውያን መሪዎች የሚዘባበቱበት እና አለፍ ሲልም ለአፍሪካ ህብረት መቀመጫነትም ሆነ ለአህጉራዊ መዲናነት አትመጥንም የሚል መከራከሪያ የሚያነሱባት እንደነበረች የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው፡፡

በብልፅግና ፓርቲ መሪነት፣ በተለወጠ አስተሳሰብ በተደመረ አቅም እንዲሁም አካታች በሆነ ልማት፤ አዲስ አበባ ዛሬ ላይ ስሟን መስላ ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነቷንም አሳድጋለች፡፡

የተጎሳቆለ መልኳን መቀየር ባስቻሉ የከተማ ኮሪደር ልማት ስኬታማ ስራዎች እንዲሁም ሰፋፊና ሰው ተኮር በሆኑ የልማት ስራዎቿ ኢትዮጵያውያንን በማኩራት መላ አፍሪካውያንን ያነቃቃችው፣ በጉስቁልናዋ ያዉቃት የነበረዉን ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ጭምር እያስደመመች የምትገኘው አዲስ አበባ በወንዝ ዳርቻ መልሶ ማልማት ስራዎቿም አርዓያ የመሆን እና የተሞክሮ ማዕከልነት አድማሷን በማስፋት አስመስክራለች፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዘርፍ፣ የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አመራሮችን ጨምሮ የሁሉም ክልሎች የዘርፉ ሃላፊዎች 2018 . የመጀመሪያ ስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ህምገማ መድረክን ካጠናቀቁ በኋላ በአዲስ አበባ አስተዳደር እየተገነባ የሚገኘዉን የቀበና ወንዝ ዳር መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።

ይህን የመሰሉ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች የከተማችንን ወንዞች ህልውና በመታደግ የቱሪስት መዳረሻ እንዲሆኑ ከማስቻላቸውም ባሻገር ምንም አይነት መሰረተ ልማት ባልነበረባቸው አካባቢዎች እንዲሁም ከዚህ ቀደም የስጋት ምንጭ በነበሩ፣ የዘመሙ መኖሪያ ቤቶች ዉስጥ ነዋሪ የነበሩ የበርካታ ዜጎችን ህይወት መታደጋቸውን በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ //ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስዩም ከበደ አስረድተዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎች በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በውስን ቦታ ላይ ከፍተኛ ምርት እያስገኘ የሚገኘውን ዘመናዊ የከተማ ግብርና እንዲሁም የሌማት ቱሩፋት እንቅስቃሴዎችንም ተዟዙረው የተመለከቱ ሲሆን ምርጥ ተሞክሮዎችን እንደ ሀገር ለማስፋት በማስቻል የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party