Prosperity Party

ሴቶች ከአባልነት ባለፈ የውሳኔ ሰጭነት ሚና እንዲኖራቸዉ እየተሠራ ነው

ጥር 04 2018 ዓ.ም

የብልፅግና ፓርቲ ዋና /ቤት የሴቶች ክንፍ የ2018 ዓ.ም እቅድ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀም ላይ ጥልቅ ግምገማ በማድረግ 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ዕቅድ ዙሪያ ከተወያየ በኋላ የም/ቤት መደበኛ ጉባኤ በማካሄድ እንዲሁም  ሌሎች ተጓዳኝ አጀንዳዎችን በመዳሰስ በስኬት ተጠናቋል፡፡

እስካሁን የተገኙ ስኬቶች፣ የታዩ ክፍተቶች እንዲሁም በቀጣይ ግማሽ ዓመት ትኩረት ተደርጎ ሊሰራባቸዉ የሚገባ ተብለዉ የተለዩ አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተካሄደ ሲሆን የእቅድ አፈፃፀም ግምገማዉ የሴቶችን ተሳትፎ፣ አመራርነት እና ተጠቃሚነት ለማጠናከር በሚያስችል መልኩ በእቅድ የተመሩበውጤት የሚመዘኑ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን እንደሚያሳይም ተገልጿል።

ፓርቲዉን የሴቶች ክንፍ ተቋማዊ አደረጃጀት በማጠናከር የሴቶችን ተጠቃሚነትና አበርክቶ ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ሴቶች በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ ማድረግ የሚችሉበትን መደላድል ለመፍጠር እንዳስቻለም በመድረኩ ተነስቷል።

የአደረጃጀቱ ፕሬዝዳንት  / ዘሃራ ኡመድ  እንደገለፁት የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ የሴቶችን ሁለንተናዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለማዳበር የሚያስችሉ ስራዎችን በመስራትና በርካቶችንም በሌማት ትሩፋት ስራዎች በማሳተፍ ከኑሮ ዉድነት ጋር በተያያዘ ሊያጋጥማቸዉ የሚችለዉን ኢኮኖሚያዊ ጫና ለማቃለል ያስቻሉ ተጨባጭ ውጤቶችን ለማስመዝገብ እንደተቻለ ገልፀዋል። አያይዘዉም፤ ሴቶች ከአባልነት ባለፈ የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ የሚያስችል ብቃት ያላቸው አንዲኾኑ እና በውሳኔ ሰጭነት አቅም ስፍራን እንዲይዙ እየተሠራ እንደኾነም አስገንዝበዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ምክትል  ፕሬዝደንትና የጽ/ቤቱ ኃላፊ  / መስከረም አበበ  በበኩላቸው በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ እና በማህበራዊ ዘርፎች የሴቶችን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አፅንኦት ሰጥተዋል፡፡

ሁለንተናዊ ሰላምን እዉን ለማድረግ የሴቶች ሚና የጎላ እንደሆነ በማስታወስ፤ 7ኛዉንሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን በማስቻል ረገድ አመራሮችም ሆኑ አባላት እንዲሁም መላዉ የሃገራችን ሴቶች የሚጠበቅባቸዉን ሀገራዊ ሃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው እና በምርጫው ሂደቶች ሁሉ ይህንኑ አጉልተዉ ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው አደራ ብለዋል። የፀናች እና የበለጸገች ኢትዮጵያ በሚል መሪ ቃል ከጥር 12/2018 . እስከ የካቲት 12/2018 . ድረስ ለአንድ ወር የሚቆይ 8 ሚሊዮን አባላት እና ደጋፊ ሴቶች የሚሳተፉበት የንቅናቄ መድረክ እንደሚያካሂድም ገልጸዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝደንት / ጠይባ ሀሰን በበኩለካቸዉ፤ ሴቶችን በፓለቲካ አመራርነት ወደ ፊት እንዲመጡ በማስቻልም ሆነ ጠንካራ እና ሁሉን አቀፍ ሀገረ-መንግስት የመገንባት ሂደቱ ላይ ጠንካራ ተሳትፎ እንዲኖራቸው በማድረግ የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ሚናውን በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party