Prosperity Party

"በሴቶች ተሳትፎ የፀናች እና የበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ በሁሉም ክልሎች እየተካሄደ ነዉ

"በሴቶች ተሳትፎ የፀናች እና የበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ በሁሉም ክልሎች እየተካሄደ ነዉ።

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን  እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ"፦በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል።

በምስራቅ ወለጋ ዞን በመድረክ  የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አሰለፈች ታደሰ የተገኙ ሲሆን ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር በኢኮኖሚ፣በፖለቲካና በማህበራዊ መስክ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት መቻሉን ገልጸዋል።

 ወ/ሮ አሰለፈች አክለው የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል እና ኢትዮጲያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር የሁሉም ሴቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በተለይ የለውጡ ተቋዳሽ የሆኑ ሴቶች  ከፍታችን ባለው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ድርብ ኃላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

"በሴቶች ተሳትፎ የፀነችና የበለፀገች ኢትዮጵያ!! - በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party