Prosperity Party

የፓርቲ ስራዎችን በተቀናጀና በተናበበ መንገድ ለመፈፀም በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር መመራት ይገባል - አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር

 

የብልፅግና ፓርቲ የፓርቲ ስራዎችን በ2018 በጀት አመት በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

የብልፅግና ፓርቲ የፓርቲ ስራዎችን በ2018 በጀት አመት በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት ተግባራዊ ለማድረግ የስትራቴጂክ ስራ አመራር የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ አስተባባሪነት የዋና ፅ/ቤት የሁሉም ዘርፎች አመራሮች በተገኙበት የውይይት መድረክ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት በሚኒስትር ማዕረግ የስትራቴጂ ስራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር፥

የፓርቲ ስራዎችን በተቀናጀና በተናበበ መንገድ ለመፈፀም በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር መመራት ይገባል ብለዋል።

የብልፅግና ፓርቲ የ10 አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ከግብ የሚያደርሱ ዋና ዋና ተግባራት በስርዓት መምራት የቀጣይ አመት ዋና ትኩረት መሆኑን የገለፁት አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር በአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር አፈፃፀም የድሬዳዋ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ፅ/ቤት የምዘና ስርዓት ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን ተናግረዋል።

ፓርቲው በስትራቴጂክ ዕቅድ መነሻ ግዙፍ ሀገራዊ ስኬቶችን አስመዝግቧል ያሉት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም የሱፍ በከተማ አስተዳደሩ አንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር በመከተል በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ መቻሉን አብራርተዋል።

በአንድ ተቋም ውስጥ የምዘና ስርዓት ማዘመን ለአንድ ተቋም ስኬታማነት ወሳኝነት አለው ብለዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ መሆኑ በውይይቱ ወቅት የተመላከተ ሲሆን የ2018 ዓ.ም በጀት አመት ዋና ትኩረት እያንዳንዱ አመራር የተግባር አፈጻጸም በአሰራሩ መሰረት መመዘን እንዳለበት ተገልጿል።

የአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር የተቋም አመታዊ ሪፖርት አዘገጃጀት ግልፅ የሚያደርግ፤ የተቋምን ስትራቴጂካዊ ግቦች ለመቅረፅ የሚያስችል ነው።

የአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ተጨባጭ ውጤቶችን አስመዝግቧል።

በዚህም ጊዜ፣ ጉልበትና ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም አስችሏል፤ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ከወረቀት ነፃ አሰራር መከተል ተችሏል።

በተጨማሪም የተቋማትንና የአመራሮችን አፈፃፀም ግልፅ በሆነ መንገድ ለመገምገም ረድቷል፤ እቅድና ሪፖርት ወቅቱን ጠብቆ እንዲዘጋጅ ተደርጓል።

የአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር ከዚህ ቀደም የሚስተዋለውን የውሸትና የተጋነነ አፈፃፀም ሪፖርት ለማስቀረትና ተጨባጭ አፈፃፀም ለመገምገም ያስችላል።

የአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት አሰራር ተግባራዊነት በከተማ አስተዳደሩ የመንግስትና የፓርቲ መዋቅሮች የመስክ ምልከታ ይደረጋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party