Prosperity Party

የድህረ እውነት ዘመን በእውነትና በእውቀት በሚል መሪ ቃል ለሲዳማ ክልል አመራሮች እና የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙያዎች የተዘጋጀው ስልጠና መካሄድ ጀመረ፡፡

በብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ አስተባባሪነት "የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀትና በእውነት" በሚል መሪ ቃል ለሲዳማ ክልል አመራሮች እና የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለሙዎች የተዘጋጀው ስልጠና በሀዋሳ ከተማ መሰጠት ጀምሯል፡፡

በስልጠና መድረኩ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ.ር) በሕዝቦች መካከል አንድነት፣ መቀራረብ፣ ወንድማማችነት/ እህትማማችንት ታሪካዊና ትርክታዊ ትስስር እየጠነከረ መጥቶ ኢትዮጵያ አንገቷን ቀና እያረገች ትገኛለች ብለዋል፡፡

በድሀረ እውነት ዘመን አፍራሽ ሃይሎች ሆን ተብሎ ስሜት ቀስቃሽ ንግግሮች በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አንድነትና ወንድማማችነት/ እህትማማችነት እሴት ለማፍረስ እየሰሩ በመሆኑ በእውነትና በእውቀት መመከት ይገባል ብለዋል፡፡

አመራሩና ባለሙያው የድህረ እውነት ዘመንን ተረድቶ እውነትንና እውቀትን በመጨበጥ ሆን ተብለው ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨትና አገር ለማፈራስ በውስጥና በውጭ የሚቀነባበሩ የሀሰት መረጃዎችን መመከት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ማርሻሎ በበኩላቸው አገራዊ ጥቅምና ክብር በማስቀድም የሚከፈቱብንን የሀሰት መረጀዎችን በእውነትና በእውቀት መታገል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ያስመዘገባቸውን ድሎችን ለሕዝብ በሚገባ ማስተዋወቅ ይገባልም ብለዋል፡፡

ዘመኑና ቴክኖሎጂ የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ ለአገር ብልፅግናና ለተቋም ሪፎርም ግንባታ ማዋል ያስፈልጋል ሲሉም አክለዋል፡፡

ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party