የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀትና በእውነት በሚል መሪ ቃል ለኮሚዩኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ
የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀትና በእውነት በሚል መሪ ቃል ለኮሚዩኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት አመራሮችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ
በብልፅግና ፓርቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ አስተባባሪነት በፓርቲው የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አንቂዎች ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቋል።
በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ(ዶ/ር)፣ በብልፅግና ፓርቲ የአዲስአበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በዚሁ ወቅት በብልፅግና ፓርቲ የአዲስአበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ባስተላለፉት መልዕክት ስልጠናው ብቁና በዕውቀት የጎለበተ ባለሙያ በማፍራት ረገድ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም ሰልጣኞች ህብረብሔራዊ አንድነትን የሚያጠናክሩ፣ የብልፅግና ተምሳሌት የሆነችውን አዲስአበባን ሁለንተናዊ ለውጥ የሚያጎሉ የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ስራዎችን በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
ዘመኑን የዋጀ የኮሚኒኬሽን እና የህዝብ ግንኙነት እውቀትና ግንዛቤ መፍጠር የሚችሉ ርዕሰ ጉዳዮች የተዳሰሱበት ይህ ስልጠና ዘርፉን ለሚመሩ አመራሮችና ባለሙያዎች የላቀ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይታመናል።
ስልጠናው በቀጣይ በሁሉም ክልሎችና በአንድ ከተማ አስተዳደር የሚሰጥ ይሆናል።