Prosperity Party

የእይታ ለውጥ እና የአመራር ቁርጠኝነት የታየባቸው የአዲስ አበባ ስኬቶች

 

በፓርቲያችን የእይታ ለውጥ እና ሰው ተኮር ተግባር ተጀምሮ ስኬት የተመዘገበበት የቤቶች ልማት፤ አምራቹንና ሸማቹን ፊት ለፊት በማገናኘት የነዋሪውን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ የገበያ ማዕከላት፤ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች የእይታ ለውጥ እና የአመራር ቁርጠኝነት የታየባቸው የአዲስ አበባ ስኬቶች ናቸው።

የብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና የወሰዱ ከፍተኛ አመራሮች በፓርቲው መሪነት በከተማው በተግባር የተሳኩ የልማት ተግባራትን ተመልክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በመዲናዋ ህዝብን በማሳተፍ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ውጤት አምጥተዋል፡፡

በዚህም አዲስ አበባን በአፍሪካ ተጠቃሽ ያደረገ ውጤቶች የተገኘበት ነው ብለዋል።

በቤት ልማትና አቅርቦት ላይ የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ የተከናወኑ ስራዎች አቅርቦቱን ለማሳደግ ማስቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

በተሰሩ ስራዎች በርካታ አቅመ ደካሞች ቤት ማግኘታቸውን የገለጹት ከንቲባዋ፤ በትምህርት ቤት ምገባ መርኃ ግብር ውጤት መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡

በመዲናዋ ህጻናትንና ወጣቶችን ታሳቢ ያደረጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል ያሉት ከንቲባ አዳነች፤ መፍጠርና መፍጠን መርህን በመከተል ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party