Prosperity Party

የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ከሁሉም ክልል እና ከተማ አስተዳደሮች ለተወጣጡ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ አመራሮች ስልጠና ሰጥቷል።

ትንተናዊ ክህሎት ለአዳጊ መሪነት፤ ክህሎት መር አጀንዳ ቀረፃ፤ የብልፅግና ፖርቲ የኮሙኒኬሽን ስልቶችና መርሆች በሚሉ ርዕሶች ላይ ያተኮረ ስልጠና ነበር።

በስልጠናው መዝጊያ ላይ ተገኝተው ማጠቃለያ የሰጡት የፖርቲው የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) ብልፅግና ፖርቲ በሰራው ሰፊ የፖለቲካ ስራ በአሁኑ ጊዜ ለአገራችን ሰላምና ጸጥታ ስጋት የሆኑትን ጽንፈኝነትና አክራሪነትን እየከሰመ በአንጻሩ ደግሞ የዜጎች በሰላማዊ መንገድ የመልማት መብታቸውን ተጠቅመው እንዲለሙ እና ወንድማማችነትና እህትማማችነት እየተጠናከረ መሆኑን ገልፀዋል።

ስልጠናው የፖለቲካ አመራሩ ስራዎችን በእውቀትና ክህሎት ለመምራት የጋራ እቅድ በማውጣት አለማቀፋዊ ሁኔታን ተረድቶ በፖለቲካ ፣ በሰላም፣ በኢኮኖሚ፣ በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚታዩትን ችግሮችን ለይቶ ተንትኖ አጀንዳዎችን በመቅረፅ ከህዝቡ ጋር ተግባቦት ለመፍጠር ትልቅ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ ታምኖበታል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party