Prosperity Party

ዛሬ ጠዋት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የአፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረዋል።

ዛሬ ጠዋት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ2017 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የአፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረዋል።

መርሃግብሩ የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም አቅርቦትን በመመልከት የጀመረ ሲሆን አለም አቀፍ የኢኮኖሚ አዝማሚያ በሀገር ውስጥ ኢኮኖሚ ላይ ያለው ተፅዕኖ አጠቃላይ ምልከታ ቀርቦበታል። በመካሄድ ላይ ያለው የማክሮ አኢኮኖሚ ሪፎርም ርምጃ ወቅታዊ መረጃም ቀርቧል።

የአለም ኢኮኖሚ በ2025 በ3.3 በመቶ የሚያድግ መሆኑ የተተነበየ መሆኑም የተገለጠ ሲሆን ከሰሃራ በታች ያለውን የአፍሪካ ክፍል ጨምሮ አብዛኛው የአለም ክፍል አዎንታዊ እድገት እንደሚያስመዘግብ ተገልጧል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 8.4 በመቶ እንደሚያድግ ተተንብይዋል። ከዚህ አንፃር የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም መርሃ ግብር የተረጋጋ ሆኖ የቁጠባ እና የኢንቬስትመንት እድገትም አሳይቷል።

የውጭ እዳ ከሀገራዊ የምርት መጠን(ጂዲፒ) ያለው ምጣኔ 13.7 ከመቶ በመድረስ ትርጉም ባለው መጠን ቀንሷል። በተጨማሪም አዲስ የውጭ ምንዛሬ አሰራር መዘርጋቱም ከውጭ የሚላክ የውጭ ምንዛሪ እንዲጨምር በማድረግ የሀገራችንን የውጪ ምንዛሬ ክምችት ጨምሯል።

ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም ከግብርና፣ ከማዕድን፣ ከኢንደስትሪ እና ኤሌክትሪክ የተገኙ የውጭ ንግድ ገቢዎችም እድገት አሳይተዋል። ቡና፣ ወርቅ፣ ጥራጥሬ፣ የዘይት ምንጭ ፍሬዎች፣ አበባ እና ኤሌክትሪክ አምስቱ ቀዳሚ የውጭ ንግድ ምርቶች ሆነዋል።

ግምገማው ታላላቅ የመሠረተ ልማት እና ሌሎች ታላላቅ ፕሮጀክቶችንም አፈፃፀም ተመልክቷል። ለአብነትም ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ 98.66 ከመቶ አፈፃፀም ላይ የደረሰ ሲሆን ስድስት ዩኒቶቹም ወደ ስራ ገብተዋል። የዛሬ ጠዋቱ ግምገማ የዘላቂ የልማት ጥረቶች በተለይም አካታችነትን እንደ ቁልፍ የስኬት መለኪያ በመውስድ በመመልከት ተጠናቅቋል። ለዘላቂ ልማት ሥራ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥሩ የሥራ ተግባራትም ቀርበዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party