ወጣቶች የድህረ እውነት ዘመንን ባህሪይ በአግባቡ በመገንዘብ ለሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና መትጋት ይገባቸዋል።
ወጣቶች የድህረ እውነት ዘመንን ባህሪይ በአግባቡ በመገንዘብ ለሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና መትጋት ይገባቸዋል።
በብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ የተዘጋጀውና
በድህረ እውነት ዘመን የወጣቶች ተሳትፎ ላይ ያተኮረው ስልጠና እየተሰጠ ነው።
ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ለተወጣጡ አመራሮችና አባላት በድህረ እውነት ዘመን የወጣቶች ሚና ላይ ስልጠና በአዳማ ከተማ መሰጠት ጀምሯል።
በዚሁ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ ም/ፕሬዚዳንት እና የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ፈዲላ ቢያ ባስተላለፉት መልዕክት ወጣቶች የድህረ እውነት ዘመንን ባህሪይ በአግባቡ በመገንዘብ ለሀገር ሁለንተናዊ ብልፅግና መትጋት ይገባቸዋል ብለዋል።
የተለያዩ የኮሚዩኒኬሽን አማራጮችን በመጠቀም ኢትዮጵያ በለውጡ መንግስት ያሳካቻቸውን ድሎች በማስተዋወቅ የድህረ እውነት ዘመን የፈጠራ ወሬዎች በህዝቡ ላይ የሚፈጥሩትን ተፅዕኖ መቀነስ ያስፈልጋልም ነው ያሉት።
በሀሰት ትርክቶች የህዝብን የአብሮነት እሴቶች ለመሸርሸር የሚደረጉ የሚዲያ ዘመቻዎችን ነቅተው በመሳተፍ መከላከል አንድነትን የሚያጠናክሩ ትርክቶችን ማጉላት ይገባል ሲሉም አክለዋል።
የድህረ እውነት ዘመንን ባህርይ በአግባቡ በመረዳት ሊወሰዱ በሚገባቸው የሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን አማራጮች ዙሪያ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን መልቲሚዲያ ዳይሬክተር አቶ ፍሬዘር ግርማ ስልጠና እየሰጡ ይገኛል።
በስልጠና መርሃ ግብሩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ም/ፕሬዝዳንትና የፅ/ቤት ኃላፊ አባንግ ኩመዳንን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።