Prosperity Party

ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት እውነተኛ የፌደራል ስርዓት ለመገንባት በሰራው ስራ ሕብረ ብሔራዊ አንድነቷን የጠበቀች ሀገር እየተገነባች ትገኛለች።

ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት እውነተኛ የፌደራል ስርዓት ለመገንባት በሰራው ስራ ሕብረ ብሔራዊ አንድነቷን የጠበቀች ሀገር እየተገነባች ትገኛለች።

በብልፅግና ፓርቲ ሕዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዘርፍ አስተባባሪነት

"የድህረ እውነት ዘመን በእውቀትና በእውነት" በሚል መሪ ቃል ለሶማሌ ክልል አመራሮች፣ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ባለሙያዎች የተዘጋጀው ስልጠና በጅግጅጋ እየተካሄደ ነው፡፡

በስልጠና መድረኩ የብልፅግና ፓርቲ የሕዝብና የዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ቢቂላ ሁሪሳ (ዶ/ር) በድህረ እውነት ዘመን ሆን ተብሎ ስሜት ቀስቃሽ ንግግሮች በመጠቀም በሕዝቦች መካከል ያለውን አብሮነትና ወንድማማችነት ለማፍረስ የሚነዙ አፍራሽ አስተሳሰቦችን በመረጃ መከላከል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ባለፉት ዓመታት ሕብረ ብሔራዊ የበለጸገች አገር ለመገንባት በተሰራው ስራ እውነተኛ ፌደራሊዝም እየጎለበተ መጥቷል ብለዋል፡፡

አመራሩና ባለሙያዎች የድህረ እውነት ዘመንን ተረድተው እውነት በመያዝና እውቀት በመጨበጥ ሀሰተኛና የጥላቻ ንግግሮችን አሸንፎ መውጣት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ኢ/ር መሐመድ ሻሌ በድህረ እውነት ዘመን አፍራሽ አስተሳቦችን ለመከላከል እውነት በመያዝና እውቀት በመጨበጥ መታገል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ብልፅግና ፓርቲ ያስመዘገባቸውን ድሎችን በሚገባ ለማስተዋወቅ እውቀት በሚገባ በመጨበጥና የመረጃ የበላይነት መያዝ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

ስልጠናው ለሶስት ተከታታይ ቀናት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party