Prosperity Party

በ2017 በጀት አመት የሀገርና የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል- አቶ አደም ፋራህ

 

የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት ማጠቃለያ መድረክ አካሂዷል።

የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት የ2017 ማጠቃለያ ሪፖርት እና 2018 በጀት አመት መነሻ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል።

በዚህ ወቅት የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንደተናገሩት 2017 ዓ.ም የትጋትና የስኬት አመት ነበር።

መላው የፓርቲው አመራርና አባላት በተባበረ ክንድ ተናበው መትጋት በመቻላችን በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።

በ2017 በጀት አመት በፓርቲው በተሰሩ ስራዎች ሶስት ዋና ዋና ስኬቶች መመዝገባቸውን ያነሱት አቶ አደም ፋራህ፥ በዚህም የውስጠ ፓርቲ ጥንካሬ ጎልብቷል፤ ስትራቴጂያዊ ትብብር እና አጋርነት ተረጋግጧል፤ የሀገርና የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል።

በበጀት አመቱ ህዝብ በልማት ተጠቃሚ እንዲሆን የተሰሩ ተግባራት ውጤታማ እንደነበሩ የተገለፀ ሲሆን በሰላምና መረጋጋት ረገድ የተሰሩ ሰራዎች በሀገር ደረጃ አንጻራዊ ሰላም እንዲሰፍን አስችለዋል ብለዋል።

2018 በጀት አመት ልዩ አመት መሆኑን የገለፁት አቶ አደም፥ ሁሉም አመራርና አባላት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ ከባለፈው በጀት አመት በተሻለ ትጋት መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።

የ2017 በጀት አመት ማጠቃለያ ሪፖርት ያቀረቡት በሚኒስትር ማዕረግ የስትራቴጂክ ስራ አመራርና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር እንዳብራሩት በፓርቲው ዋና ጽ/ቤት በሚገኙ ዘርፎች በበጀት አመቱ የታቀዱ ስራዎች ግባቸውን አሳክተዋል። የተስተዋሉ ውስን ክፍተቶችም በቀጣይ በትኩረት የሚሰራባቸው እንደሆነ አመላክተዋል።

2018 በጀት አመት ዕቅድ ቀርቦም ውይይት ተደርጎበታል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party