Prosperity Party

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ሀገራዊ ለውጡ እውን የሆነበት የ8ኛ ዓመት የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል

የሰልፉ ተሳታፊ የሆኑ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በመጋቢት 24 ተምሳሌታዊ ጉዞ እና መሰረታዊ ርምጃ የተመዘገቡ ስኬቶችን እያደነቁ ነው። 

በለውጡ መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ተግባራትን በመደገፍ፣ በቀጣይም የተሻለ ስራ እንዲሰራ ከመንግሥት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ የሚያረጋግጡ መልዕክት እያስተላለፉ ይገኛሉ።

በዚህም በመጋቢት 24 ፍሬ ወደ ተምሳሌታዊ ጉዞ፣ ጠንካራ መሰረት የተምሳሌትነት ጉዞ ስንቅ፣ መሰረት ባለው ርምጃ ወደ ተምሳሌትነት፣ መጋቢት 24 የተምሳሌታዊነታችን መሰረትና መፍለቂያ ነው፣ መጋቢት 24 ሀገር ከመፍረስ የዳነችበት የታሪክ ምዕራፍ የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

በተጨማሪም የመጋቢት 24 ፍሬዎች የተምሳሌትነት ጉዞ የትውልድ ብልፅግና ነው፣ መጋቢት 24 የኢትዮጵያ ለውጥ መነሻና ብልፅግና መሠረት ነው፣ መጋቢት 24 በመስዋዕትነት መጣ በመስዋዕትነት እንጠብቀዋለን፣አብረን ጀምረናል አብረን እንደርሳለን፣ አስተሳሳሪ እና የወል ትርክታችን ለዘላቂ አንድነት እና አብሮነታችን የሚሉ መልዕክቶች እየተላለፉ ነው።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የአሶሳ ከተማ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party