Prosperity Party

"በ7ኛ ሀገራዊ ምርጫ መንታ ግብ ለማሳካት በልዩ ትኩረት ይሰራል"- አቶ ብርሃኑ ፈይሳ

የብልፅግና ፓርቲ የሀብት አስተዳደር ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር እቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ማካሄድ ጀመረ

በመድረኩ የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሀብት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ  አቶ ብርሃኑ ፈይሳ እንደተናገሩት   የ7ኛ ሀገራዊ ምርጫ መንታ ግብ ለማሳካት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ይህ ዓመት ለህዝባችን የገባነዉን ቃል በላቀ ዉጤት ተግብረን በ7ኛ ሀገራዉ ምርጫ ለአዲስ ሀላፊነት የምንዘጋጅበት በመሆኑ ምርጫዉ ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ሰላማዊ እና የህዝብ ቅቡልነት ያገኘ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በተጨማሪም ፓርቲያችን በምርጫ ብርቱ ተወዳዳሪ ሆኖ በመቅረብ የህዝቡን ድምፅ እንዲያገኝ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

ባለፉት 6 ወራቶች ዉስጥ የፓርቲው የአስራር መመሪያና ደንብ እንዲከበር እና ፓርቲውን በሚመጥን ደረጃ ሀብትን በተደራጀና ግልፅነት ባለዉ ሰራዓት እንዲመራ በማድረግ ረገድ የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡን ገልፀዋል።

ፓርቲውን በሚመጥን መልኩ የሀብት አስተዳደር እና የፋይናንስ አሰራሩን በበለጠ በማዘመን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማሳካት የተጀመረው ጉዞ እንዲሰምር በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አቶ ብርሃኑ ገልፀዋል።

በግምገማ መድረኩ ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ሪፖርት እያቀረቡ ሲሆን የተመዘገቡ ስኬቶች እና ዉስንነቶች እንዲሁም ልምድ የሚወሰድባቸው ልዩ አፈፃፀሞች ላይ በጥልቀት ከተወያዩ በኋላ የቀሪ 6 ወራቶች የስራ አቅጣጫ ይቀመጣል ተብሎ ይጠበቃል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party