Prosperity Party

ፈተናዎችን ወደ ዕድል እየለወጠ ሀገርን ያሻገረው የብልጽግና ጉዞ

ኢትዮጵያ ባለፉት የለውጥ ስምንት ዓመታት ውስጥ ያለፈችባቸው መንገዶች በበርካታ ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ ፈተናዎች የተሞሉ ነበሩ። የለውጡ መንግሥት የገጠሙትን ታላላቅ እንቅፋቶች ወደ አዳዲስ ዕድሎች በመቀየር አገርን ወደ ላቀ ብልጽግና ማሻገር የቻለ ብርቱ አመራር መፈጠሩን በተግባር አሳይቷል።

ባለፉት ዓመታት አገራችን እንደ ድርቅ፣ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ያሉ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን እንዲሁም እንደ ኮቪድ-19 ያሉ ዓለም አቀፍ ወረርሽኞችን አስተናግዳለች። ከእነዚህም ባሻገር፣አንዳንድ ጽንፈኛ ሀይሎች የፈጠሩት የውስጥ ጦርነትና ታይቶ የማይታወቅ የውጭ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች የአገሪቱን ሉዓላዊነትና አንድነት በእጅጉ ፈትነውታል። ሆኖም አመራሩ በእነዚህ ፈተናዎች ከመረበሽ ይልቅ፣ ከውስጣቸው ዕድልን ፈልቅቆ በማውጣት ለሀገራዊ ግንባታ እንዲውሉ አድርጓቸዋል።

የዚህ ጽኑ አመራርና የማይበገር ሕዝባዊ አንድነት ትልቁ ማሳያ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ነው። ኢትዮጵያ ግድቡን እንዳታጠናቅቅ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ብርቱ ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎች ቢሰነዘሩባትም፣ አመራሩ ፈተናውን ወደ ዕድል በመቀየር ግንባታው ዳር እንዲደርስ አድርጓል። ይህ ስኬት ለዓለም ያሳየው ትልቅ እውነታ ቢኖር፣ ኢትዮጵያ ምንም ዓይነት ጫና ቢኖርባትም የጀመረችውን የልማትና የብልጽግና ጉዞ የማታቆም፣ የሉዓላዊነት ምልክት መሆኗን ነው።

የዚህ በሳል አመራር ውጤት ዛሬ ላይ በግልጽ እየታየ ይገኛል። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላት የዲፕሎማሲ አቅምና የተፅዕኖ ደረጃ ከመቼውም ጊዜ በላይ አድጓል። ጫናዎችን ተቋቁሞ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማጠናቀቅ መቻላችን በዜጎች ዘንድ የማይበገር ብሔራዊ ኩራት እንዲፈጠር አድርጓል። በተጨማሪም፣ ፈተናዎችን በብቃት የመወጣት ልምዳችን በአገራችን ላይ የነበረውን የተረጂነትና የችግር ገጽታ በመቀየር፣ ኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ልማቷን የማታቆም የጽናትና የብልጽግና ተምሳሌት መሆኗን ለዓለም አስመስክሯል።

የለውጡ አመራር ችግሮችን ወደ ስኬት መሰላል በመቀየር፣ ኢትዮጵያን ከፈተናዎች ማዶ ወደሚገኘው ብልጽግና በጽኑ መሠረት ላይ እያሻገራት ይገኛል።

#prosperity

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party