የኢትዮጵያን ልማትና እድገት ማስቀጠል የሚችል ፓርቲ ለመምረጥ እየተመዘገብን ነዉ- የጉጂ ዞን ነዋሪዎች
በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በመሳተፍ የኢትዮጵያን ልማትና እድገት ማስቀጠል የሚችል ፓርቲ በድምፃቸው ለመምረጥ እየተመዘገቡ መሆናቸውን የጉጂ ዞን ነዋሪዎች ገለጹ።
ነዋሪዎቹ ሳይዘናጉ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዜጋዊ ግዴታቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን የገለጹ ሲሆን፤ ድምፃቸውንም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና ሊያረጋግጥ ለሚችል የፖለቲካ ፓርቲ ለመስጠት መወሰናቸውን ተናግረዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ምርጫው ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውንም ገልፀዋል።