Prosperity Party

ተግባራዊነቱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላትን ታሪካዊ የግንባር ቀደምትነት ሚና የሚያሳይ ነው - አቶ አደም ፋራህ


 ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ተግባራዊነት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላትን ታሪካዊ የግንባር ቀደምትነት ሚና የሚያሳይ መሆኑን አቶ አደም ፋራህ ገለፁ።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ትግበራን በዛሬው ዕለት በማስጀመር የሥጋ፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የቡና፣ ጫትና የበቆሎ እህሎች ወደ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ወደ ደቡብ አፍሪካ ልካለች።

ለስምምነቱ ተግበራዊነት በማስመልከት በተዘጋጀው መርሀግብር ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚሁ ወቅት አቶ አደም እንደገለፁት፤  የዛሬው መርሃ ግብር አዲስ ግብይት ለመጀመር ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ጉዳዮች ላይ ያላትን ታሪካዊ የግንባር ቀደምትነት ሚና በንግድና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይም በመድገም ያለንን አጋርነት ለአፍሪካዊያን ወንድሞቻችን የምናረጋግጥበት ጭምር ነው።

ሁለንተናዊ ብልጽግና የሰፈነባትን ኢትዮጵያ የመገንባት ሀገራዊ ራዕያችን በራሳችን ታጥረን ብቻ ሊሳካ አይችልም ያሉት አቶ አደም፤ እርስ በርስ የተሳሰሩ ገበያዎችን፣ ክፍትና የተሳለጠ ሎጂስቲክስና የዜጎቻችንን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶችን መፍጠር ይጠይቃል ብለዋል።

እንደ አቶ አደም ገለፃ፤ ቀጣናዊ ንግድ ኢኮኖሚያዊ ስትራቴጂ ብቻ ሳይሆን የሰላምና መረጋጋት ስትራቴጂም ነው።

ዕቃዎች በነፃነት በሚንቀሳቀሱበት ቦታ ሰዎችና ሐሳቦች ይክተላሉ  ያሉት አቶ አደም፤ በዚህም ግጭቶች የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ ትብብሮች እንደሚተኩ ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት ከማጽደቅ ወደ ተግባራዊ እንቅሰቃሴ የገባችበት እርምጃ የመንግስታችንን ቃልን በተግባር የማረጋገጥ ባህል ቀጣይነት የታየበት ነውም ብለዋል።

አክለውም የሃገራችን ብሎም የአፍሪካ መጻኢ እጣ-ፈንታ በጋራ ጥንካሬዎቻችን እና በጋራ ለመስራት ባለን ቁርጠኝነት ይወሰናልም ብለዋል።

በተጨማሪም የተጀመረውን የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ድርድርን ብሔራዊ ጥቅማችንን ባስጠበቀ መልኩ ውጤታማ ድርድር በማድረግ እንዲቋጭ  ጥረቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ አደም አሳስበዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party