Prosperity Party

የፓርቲያችን የብዛሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ አቅጣጫ ውጤታማ እየሆነ ነው - አቶ አደም ፋራህ

የብልፅግና ፓርቲ የስድስት ወራት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ከነገ ጀምሮ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ያደረጋል።

ከግምገማ መድረኩ አስቀድሞ በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና / ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የፓርቲ  አመራሮች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን የልማት ስራዎችን ምልከታ አድርገዋል።

‎‎ጥር 05 2018 ዓ.ም

አቶ አደም ፋራህና ከፍተኛ አመራሮቹ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ሲደርሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ(/) እና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በአቶ አደም ፋራህ የተመራው ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል አመራሮች በቡታጅራ ከተማ የአቮካዶ ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል፣ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት፣ ቀሸት ንብ ማነብ ስራ ማህበር እና ደስታ ጋርመንትን ምልከታ አድርገዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ከጉብኝቱ በኋላ በሰጡት አስተያየት በዞኑ የፓርቲያችን የብዝሀ ዘርፍ ኢኮኖሚ አቅጣጫ ውጤታማ ነው ብለዋል።

በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በኮሪደር ልማትና በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች የፓርቲያችን እሳቤዎች ገቢራዊነቱ በሁሉም መስክ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።

በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ምርቶችን በማምረት ኤክስፐርት እያደረጉ ያሉ ድርጅቶችን መመልከት ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ዘርፍ እያደረገች ላለችው ሽግግር ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በብዝሀ ዘርፍ የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሀገርን ኢኮኖሚ ከመደገፍ ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል ተፈጥሯል ነው ያሉት።

ዞኑ በተመሰረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የልማት ስራዎች ላስመዘገበው የተሻለ ውጤት አመራሩንና ህብረተሰቡን አመስግነዋል።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party