የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀት እና በእውነት ለመምራት ጊዜውን የሚመጥን የኮሚዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት እውቀትና ግንዛቤ ያስፈልጋል
በብልፅግና ፓርቲ የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ለፓርቲው የኮሚዩኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት አመራሮች እና ባለሞያዎች እየተሰጠ ያለው ስልጠና ዛሬም ቀጥሏል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት የህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አንቂዎች "የድህረ እውነት ዘመንን በእውቀት እና በእውነት" በሚል ርዕስ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።
የዕለቱ መርሀ ግብር ''የሚዲያ ክትትል፣ ትንተና እና የሚዲያ ዳሰሳ'' እና "መረጃ ማጣራትና የቀውስ ጊዜ ኮሚዩኒኬሽን" ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን መምህርና ተመራማሪ አንተነህ ፀጋዬ (ዶ/ር) ስለሚዲያ ክትትል፣ ትንተና እና የሚዲያ ዳሰሳ እያሰለጠኑ ይገኛል።
ስልጠናው በቀጣይ በሁሉም ክልሎችና በአንድ ከተማ አስተዳደር የሚሰጥ ይሆናል።