Prosperity Party

የኢትዮጵያ እዉነት: የነገዉ ተስፋ:- የገበታ ለትዉልድ ድንቅ ስጦታ

ትናንት በሐሳብ ዘር ውስጥ የተጸነሱት፣ ዛሬ በምድር ላይ አብበው እና ፈክተው ፍሬ አሽተው እያፈሩ ያሉት! የ"ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የተደበቀ ውበት እንዲሁም የተዘነጋ የታሪክ እና የተፈጥሮ ሀብት እየገለጡ ለዓለም እያስተዋወቁ ያሉ የጥበብ እና የዕይታ ጉልበት ውጤቶች ናቸው። 

እነዚህ ፕሮጀክቶች ከንድፍ ጀምሮ እስከ አፈጻጸም የተመሩበት ፍጥነት እና ጥራት፣ ቅልጥፍና እና ትብብር "የማይቻል የለም" የሚለው አዲሱ የኢትዮጵያውያን የሥራ ባህል በተግባር የታየበት ነው። 

እስካሁን የተመረቁት ደንቢ ኢኮ ሎጅ፣ ሸበሌ ሪዞርት እና ዛሬ የተመረቀውን ሎጎ ሐይቅ ሪዞርትን ጨምሮ ስምንት የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች በሀገር ደረጃ ተይዘዋል። 

በእነዚህ ፕሮጀክቶች ሀገራችን ካሏት የተፈጥሮ ጸጋዎች ባሻገር፣ ሰው ሠራሽ ውበቶችን በማከል የቱሪዝም አድማሷን እያሰፋች ትገኛለች። 

ይህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሣሽነት የተጀመረው ታላቅ ንቅናቄ፣ ትውልድ የሚረከበው ታሪክ ብቻ ሳይሆን ትውልድ የሚኖርበትን እና የሚኩራራበትን ሀገር የመገንባት ጥበብ ነው።

እነዚህ ፕሮጀክቶች ከመዝናኛነት ባለፈ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ አላቸው፦

• ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፦ ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር እና የቱሪዝም ገቢን በማሳደግ።
• ሀገራዊ ገጽታ፦ የኢትዮጵያን ድንቅ ገጽታ ለዓለም አቀፍ ጎብኚዎች በላቀ ደረጃ በማስተዋወቅ።
• የተስፋ አሻራ፦ ነገን የሚያሳምሩ እና ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፉ ተጨባጭ ሀብቶችን በማፍራት። 

በእውነትም "ገበታ ለትውልድ" የተቀበረ ታሪክን እየገለጠ፣ የኢትዮጵያ የብልጽግና ተስፋ የሚጨበጥ እና የሚከናወን መሆኑን በተግባር ያሳየ የትውልድ ስጦታ ነው! 

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party