Prosperity Party

"ብልጽግና ፓርቲ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እመርታዊ ድሎችን ያስመዘገበ ፓርቲ ነዉ”- ወ/ሮ መስከረም አበበ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት አስተባባሪነት "በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል የማጠቃለያ በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል የተለያዩ ከተሞች እየተካሄደ ይገኛል።

መድረኩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት አስተባባሪነት በየደረጃው ሲካሄዱ የቆዩ የዉይይት መድረኮች ማጠቃለያ እንደሆነ ተገልጿል።
 
የመድረኩ የማጠቃለያ መርሃ ግብር በክልሉ ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ እና ዲላ ከተሞች እየተካሄደ ሲሆን የመድረኩ አካል የሆነዉ የእግር ጉዞ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።
 
የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መስከረም አበበ "በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው መድረክ በሀገር ደረጃ ከ 8 ሚሊዮን በላይ ሴቶች ተሳታፊ መሆናቸውን ተናግረዋል።
 
መድረኩ በ 7ተኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ላይ መግባባት በመፍጠር ሴቶች በምርጫዉ ሂደት የበኩላቸውን እንዲወጡ ያለመ መሆኑን ገልፀዋል።
 
በተጨማሪም ሴቶች በኢኮኖሚ፣ ፖለቲካ፣ ማህበራዊና የዉጭ ግንኙነት መስኮች የተመዘገቡ አስደናቂ ዉጤቶችን በማስገንዘብ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ግልፅነት ለመፍጠር እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።
 
ብልጽግና ባለፉት የለዉጥ ዓመታት የሴቶችን ተሳትፎና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በኩል እመርታዊ ድሎችን ያስመዘገበ ፓርቲ መሆኑን ወ/ሮ መስከረም አስረድተዋል።
ከመድረኩ ጎን ለጎን የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የስራ መፍጠሪያ ኢንሼቲቮች ተግባራዊ የተደረጉ ሲሆን 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተአማኒና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በብልጽግና ፓርቲ የበላይነት እንዲጠናቀቅ የሴቶች ክንፍ አባላት ያለባቸውን ድርብ ተልዕኮ እንዲወጡ ጠይቀዋል።
 
የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ እታገኝ ኃ/ማርያም በከተማው በ 63 አደረጃጀቶች ከ 16 ሺ በላይ የሴቶች ክንፍ አባላት እንዳሉ ገልፀዋል።
 
በከተማው ሴቶች በሁሉም መስኮች ተደራጅተዉ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ ነዉ ብለዋል።
 
በመድረኩ "በሴቶች ተሳትፎ የፀናችና የበለፀገች ኢትዮጵያ !!" በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ ሰነድ ቀርቦ ዉይይት እየተደረገበት ይገኛል።
 
በመድረኩ በየደረጃዉ የሚገኙ የብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ ከወላይታ ሶዶ ከተማ የተወጣጡ ግንባር ቀደም ሴቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በብዛት የታዩ ዜናዎች

News Card List
Prosperity Party